+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ يَقُمْ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ»

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 35]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 35]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በረመዳን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ የምትገኘው መወሰኛይቱ ሌሊትን (ለይለቱል ቀድርን) የመቆም ትሩፋትን ተናገሩ። በዚህች ሌሊት በሷና ስለሷ ትሩፋት በመጡ ሐዲሦች አምኖ እንዲሁም በስራው ይዩልኝና ይስሙልኝን ሳይሆን የአላህን ምንዳ ከጅሎ በሶላት፣ በዱዓእ፣ ቁርአን በመቅራትና በዚክር የታገለ ሰው ያለፈውን ኃጢዓቱ ይማራል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የመወሰኛይቱ ሌሊት (የለይለቱል ቀድር) ትሩፋትና ይህቺን ሌሊት መቆም ላይ የሚበረታታ መሆኑ፤
  2. መልካም ስራዎች ከእውነተኛ ኒያ ጋር ካልሆነ በቀር ተቀባይነት አያገኙም።
  3. የመወሰኛይቱ ሌሊትን (የለይለቱል ቀድርን) አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ለሱ መማሩ የአላህን እዝነትና ትሩፋት እንረዳበታለን።
ተጨማሪ