+ -

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ رِجَالًا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أُرُوا لَيْلَةَ القَدْرِ فِي المَنَامِ فِي السَّبْعِ الأَوَاخِرِ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَرَى رُؤْيَاكُمْ قَدْ تَوَاطَأَتْ فِي السَّبْعِ الأَوَاخِرِ، فَمَنْ كَانَ مُتَحَرِّيهَا فَلْيَتَحَرَّهَا فِي السَّبْعِ الأَوَاخِرِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2015]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"የተወሰኑ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ባልደረባዎች በህልማቸው ለይለቱል ቀድር በመጨረሻው የረመዷን ሰባቱ ቀናት መሆኗን ተመልክተዋል። የአላህ መልክተኛም(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ "በህልማችሁ በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ሆና ማየታችሁ ህልማችሁ ከእውነታው ጋር ገጥማለች ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ለይለቱል ቀድርን የሚፈልግ የሆነ ሰው በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ውስጥ ይፈልጋት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2015]

ትንታኔ

ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ባልደረቦች የተወሰኑት ለይለቱል ቀድር በረመዷን የመጨረሻዎቹ ሰባት ሌሊቶች ሆና በህልማቸው ተመለከቱ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ለይለቱል ቀድርን በህልማችሁ በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ሆና ማየታችሁ ህልማችሁ ከእውነታው ጋር ገጥማለች ብዬ አምናለሁ። እርሷን ያሰበና ለመፈለግ የጓጓ ሰው በነዚህ ምሽቶች እርሷን ፍለጋ መልካም ስራዎችን በማብዛት ይታገል። እርሷ በመጨረሻዎቹ ሰባት ሌሊቶች እንደምትሆን ተስፋ ይደረጋልና።" ያ ማለት የረመዷን ቀናቶች ሰላሳ የሆኑ ጊዜ ከሀያ አራተኛው ምሽት ይጀምራል። የረመዷን ቀናቶች ሀያ ዘጠኝ የሆኑ ጊዜ ደግሞ ከሀያ ሶስተኛው ሌሊት ይጀምራሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الصربية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የለይለቱል ቀድር ደረጃና እርሷን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ከአላህ ጥበብና እዝነት መካከል ሰዎች እርሷን ፍለጋ በአምልኮ ሲታገሉ ምንዳቸው እንዲጨምር ይህቺን ሌሊት መደበቁ ነው።
  3. ለይለቱል ቀድር በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ነው። በመጨረሻዎቹ ሰባት ሌሊት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ተስፋ ይደረግበታል።
  4. ለይለቱል ቀድር ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ሌሊቶች መካከል አንዷ ሌሊት ናት። ይህቺም ሌሊት አላህ ዐዘ ወጀል ቁርአንን በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ያወረደባት፤ በረከቷን ከአንድ ሺህ ወር የተሻለ ያደረጋት፤ ደረጃዋን ከፍ ያደረጋትና መልካም ስራ መስራት ተመራጭ ያደረገባት ምሽት ናት።
  5. (ለይለቱል ቀድር) ተብላ የተጠራቸው ወይ ልቅና ከሚለው ቃል ተወስዶ ነው። (እከሌ ቀድሩ ትልቅ ነው።) ማለትም ልቅናው ከፍ ያለ ነው ማለት ነው። ልክ እንደዚሁ ቀድሯ ትልቅ የሆነችው ሌሊት ሲባል "ቀድር" የሚለው ቃል ሌሊት ለሚለው ቃል ገላጭ ይሆናል። ማለትም የላቀችዋ (የተከበረችው) ምሽት ማለት ነው። ማለትም ደረጃዋ፣ ልቅናዋና ስፍራዋ የላቀ ማለት ነው። {እኛ (ቁርአንን) በተባረከው ምሽት አወረድነው።} [አድዱኻን:3] ወይም ደሞ (ተቅዲር) መወሰኛ ከሚለው ቃል ነው የተወሰደችው ቢባልም ያስኬዳል። ማለትም በዚህች ምሽት ውስጥ በአመት ውስጥ የሚከሰተው ነገር ይወሰናል። {በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል።} [አድዱኻን:4]