عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«تَحَرَّوْا لَيْلَةَ القَدْرِ فِي الوِتْرِ مِنَ العَشْرِ الأَوَاخِرِ مِنْ رَمَضَانَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2017]
المزيــد ...
ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2017]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለይለቱል ቀድርን ለመፈለግ መልካም ስራዎችን በማብዛት መታገል እንደሚገባ አነሳሱ። ለይለቱል ቀድርም በሁሉም ዓመት ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት በጎዶሎው ምሽቶች መሆኗ ተስፋ ይደረጋል። እነርሱም: ሀያ አንደኛ፣ ሀያ ሶስተኛ፣ ሀያ አምስተኛ፣ ሀያ ሰባተኛና ሀያ ዘጠነኛ ሌሊቶች ናቸው።