+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ رَضِيَ اللهُ عَنْهَا قَالَتْ:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا دَخَلَ الْعَشْرُ أَحْيَا اللَّيْلَ، وَأَيْقَظَ أَهْلَهُ، وَجَدَّ وَشَدَّ الْمِئْزَرَ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1174]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1174]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ምሽቱን ሁሉ በተለያዩ አምልኮዎች ህያው ሆነው ያሳልፉ ነበር። ቤተሰባቸውንም ለሶላት ይቀሰቅሱ ነበር። ከልማዳቸው ተጨማሪ በሆነ መልኩ በአምልኮ ይታገሉ ነበር። ከሚስቶቻቸው ጋር መተኛትንም ትተው በአምልኮ ብቻም ያሳልፉ ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በላጭ የሆኑ ወቅቶችን በመልካም ስራ ላይ ሆነን እንድናሳልፍ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በረመዷን የመጨረሻ አስሩ ቀናቶች አምልኮ መጨመርና ሌሊቱንም በአምልኮ ህያው ሆኖ ማሳለፍ እንደሚወደድ ያስረዳናል።"
  3. አንድ ባሪያ ቤተሰቦቹን ወደ አምልኮ በማዘዝ ላይ ጥረት ሊያደርግና በዛም ላይ ሊታገስ ይገባዋል።
  4. መልካም ተግባራትን መስራት ቆራጥነትን፣ ትግስትንና መበረታታትን ይፈልጋል።
  5. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ዑለማዎች (ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር) በሚለው ትርጉም ዙሪያ የተለያየ ሃሳብ አላቸው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሌላው ጊዜ በተለየ ልምዳቸው ጨምረው በማምለክ መታገላቸውን ለመግለፅ ነው፤ ያሉም አሉ። ትርጉሙ ለአምልኮ መታጠቃቸው ነው። "ለዚህ ጉዳይ ሽርጤን አጠበቅኩኝ።" ሲባል ለርሱ ታጠቅኩኝ ተዘጋጀሁ ማለት ነው፤ ያሉም አሉ። በአምልኮ ለመጠመድ ሴቶችን መራቃቸውን ለመግለፅ የተጠቀሙት ቃል ነውም ተብሏል።