+ -

عَنْ جَرِيرٍ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ يُحْرَمِ الرِّفْقَ يُحْرَمِ الْخَيْرَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2592]
المزيــد ...

ከጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2592]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው በዲናዊ፣ በዱንያዊ፣ ለራሱ በሚሰራቸው፣ ከሌሎች ጋርም ባለው ጉዳዮች ለስላሳነትን ያልተገጠመ (ያልታደለ) ሰው በርግጥም መልካምን ሁሉ እንደተነፈገ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የለስላሳነት ትሩፋትን፣ እርሱን በመላበስ መነሳሳቱንና ድርቅና መወገዙን እንረዳለን።
  2. በለስላሳነት የሁለቱም ሀገር ስርአት መስተካከልና የሁለቱም ሀገር ጉዳዮች መቅለል ሲገኝ በድርቅና ግን የዚህ ተቃራኒ ነው የሚገኘው።
  3. ለስላሳነት ከመልካም ስነምግባርና ከሰላማዊነት የሚመነጭ ሲሆን ድርቅና ደግሞ ከቁጡነትና ከመጥፎ ስነምግባር የሚመነጭ ነው። ለዚህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን አወደሱም እጅግም አሞካሹት።
  4. ሱፍያን አሥሠውሪይ አላህ ይዘንላቸውና ለባልደረቦቻቸው "ለስላሳነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሉ። ቀጥለውም "እርሱም ሁሉንም በቦታቸው ማስቀመጥ ነው። ብርቱነትን በቦታው፣ ልስላሴን በቦታው፣ ሰይፍን በቦታው፣ አለንጋን በቦታው ማስቀመጥ ነው።" አሉ።