عن أبي ذر رضي الله عنه قال: قال لي النبي صلى الله عليه وسلم:
«لَا تَحْقِرَنَّ مِنَ الْمَعْرُوفِ شَيْئًا، وَلَوْ أَنْ تَلْقَى أَخَاكَ بِوَجْهٍ طَلْقٍ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2626]
المزيــد ...

ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ:
"ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2626]

ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካምን ከመፈፀም እንዳናሳንስ አነሳሱን። ከነዚህ መካከልም ከሙስሊም ጋር በሚገናኝ ወቅት በፈገግታ ፊትን መፍታት ይጠቀሳል። አንድ ሙስሊም ይህን በመፈፀሙ ምክንያት ሙስሊም ወንድሙን ማዝናናትና በውስጡ ደስታን መጨመር ስለሚያመጣ በዚህ ላይ ሊጥር ይገባል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. በአማኞች መካከል መዋደድ፣ ሲገናኙ ፈገግ ማለትና ማበሰር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  2. ሸሪዓ ለሙስሊሞች በሚጠቅምና ህብረታቸውን አንድ በሚያደርግ ነገር ሁሉ መምጣቱ የዚህ ሸሪዓን ምሉዕነትና ጠቅላይነት ያስረዳናል።
  3. ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
  4. በሙስሊሞች መካከል አንድነትን ስለሚያረጋግጥ በሙስሊሞች ላይ ደስታን መጨመር ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (68)