عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«كان رجلٌ يُدَايِنُ الناسَ، فكان يقول لفتاه: إذا أتيتَ مُعسِرًا فتجاوز عنه، لعل اللهَ يَتجاوزُ عنا، فلقي اللهَ فتجاوز عنه».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡
"ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን የተቸገረ ካጋጠመህ እለፈው።' አላህንም ተገናኘ፤ አላህም ይቅር አለው።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ ﷺ ሰዎች ጋር በመበዳደር የሚንቀሳቀስ ወይም በዱቤ የሚሸጥላቸው ስለሆነ ሰው ተናገሩ። ለሰዎች ያበደረውን ብድር ለሚቀበልለት ሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ "ተበዳሪ ዘንድ ስትሄድ እዳውን መክፈል ተስኖት ካገኘሀው እለፈው" ይህም የሚከፍልበትን ፋታ በመስጠት፣ እዳውን በመፈለግ ላይ ችክ ባለማለት ወይም ጥቂት ቢጎድልም ያለውን በመቀበል ሊሆን ይችላል። ይህንንም የሚያደርገው አሏህ የእርሱንም ወንጀል እንዲያልፍለትና ይቅር እንዲለው ከመከጀል አኳያ ነበር። በሞተም ጊዜ አሏህም ማረው፤ ወንጀሉንም ይቅር አለለት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሰዎች ጋር ባለ መስተጋብር መልካሙን መዋል፣ ይቅር ማለትና ሰው ሲቸግረው ብድሩን ማለፍ አንድ ባርያ በቂያማ እለት ከሚድንባቸው ትላልቅ ሰበቦች መካከል እንደሆነ፤
  2. ለፍጡራን በጎ መዋል፣ ለአሏህ ስራን ጥርት ማድረግና እዝነቱንም መከጀል ለወንጀል መሀርታን ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል መሆኑን እንረዳለን።