عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إِنَّ الْمُقْسِطِينَ عِنْدَ اللهِ عَلَى مَنَابِرَ مِنْ نُورٍ، عَنْ يَمِينِ الرَّحْمَنِ عَزَّ وَجَلَّ، وَكِلْتَا يَدَيْهِ يَمِينٌ، الَّذِينَ يَعْدِلُونَ فِي حُكْمِهِمْ وَأَهْلِيهِمْ وَمَا وَلُوا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1827]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው። (ፍትሃዊ የሚባሉትም) እነዚያ በፍርዳቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና በተሾሙበት ጉዳዮች ላይ ፍትህን የሚያሰፍኑ ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1827]
እነዚያ በአመራራቸውና በፍርዳቸው ስር ያሉ ሰዎችን እና በቤተሰቦቻቸው መካከል በፍትህና በእውነት የሚፈርዱ ሰዎች የትንሳኤ ቀን ለነሱ ክብር ይሆን ዘንድ ከፍ ባሉ ከብርሃን የተፈጠሩ ወንበሮች ላይ እንደሚቀመጡ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። እነዚህም ወንበሮች በአርራሕማን ቀኝ በኩል የሚገኙ ናቸው። ጥራት የተገባው አላህ ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው።