+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَ:
«أَحَبُّ الْبِلَادِ إِلَى اللهِ مَسَاجِدُهَا، وَأَبْغَضُ الْبِلَادِ إِلَى اللهِ أَسْوَاقُهَا».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 671]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 671]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች እንደሆኑ ተናገሩ። ይኸውም የአምልኮ ቤቶችና ምስረታቸውም አላህን በመፍራት ላይ ስለሆነ ነው። አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላውም ስፍራ ገበያዎች እንደሆኑ ተናገሩ። ይኸውም በአብዛኛው ማታለል፣ መሸወድ፣ ወለድ፣ የውሸት መሃላ፣ ቃልን ማፍረስና አላህን ከማስታወስ ችላ የሚባልበት ስፍራ ስለሆነ ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የመስጂዶች ክብርና ደረጃን እንረዳለን። ይህም የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው ስለሆኑ ነው።
  2. የአላህን ውዴታ በመፈለግ መስጂዶችን አዘውትሮ በመያዝ ላይ፣ ወደ መስጂድ አብዝቶ በመመላለስ ላይና ወደ ገበያዎች ደግሞ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር በአላህ ወደመጠላት የሚያደርሱ ሰበቦች ላይ ከመውደቅ ለመራቅ ሲባል አብዝቶ ባለመመላለስ ላይ መነሳሳቱን እንመለከታለን።
  3. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "መስጂዶች የአላህ እዝነት የሚወርድባቸው ስፍራዎች ሲሆኑ ገበያዎች ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ ናቸው።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ