عن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الْآخِرُ، يَقُولُ: «مَنْ يَدْعُونِي فَأَسْتَجِيبَ لَهُ؟ مَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ؟ مَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ؟».
[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'"
Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]
የጠራውና ከፍ ያለው አላህ በሁሉም ሌሊት የሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ በመውረድ ባሮቹ እንዲለምኑት እንደሚያነሳሳ፤ እርሱ ለለመነው ተቀባይ፤ ለጠየቀው ሰጪ ነውና፤ የሚፈልጉትን እንዲጠይቁት የሚያነሳሳ፤ እርሱ ለአማኝ ባሮቹ መሀሪ ነውና ለወንጀሎቻቸውም ከርሱ ምህረትን እንዲፈልጉ የሚያብረታታቸው መሆኑን ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ገለፁ።