عَنِ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنين رَضيَ اللهُ عنها زَوْجَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
أَنَّ الْحَوْلَاءَ بِنْتَ تُوَيْتِ بْنِ حَبِيبِ بْنِ أَسَدِ بْنِ عَبْدِ الْعُزَّى مَرَّتْ بِهَا وَعِنْدَهَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقُلْتُ: هَذِهِ الْحَوْلَاءُ بِنْتُ تُوَيْتٍ، وَزَعَمُوا أَنَّهَا لَا تَنَامُ اللَّيْلَ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَا تَنَامُ اللَّيْلَ! خُذُوا مِنَ الْعَمَلِ مَا تُطِيقُونَ، فَوَاللهِ لَا يَسْأَمُ اللهُ حَتَّى تَسْأَمُوا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 785]
المزيــد ...
የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው:
«የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከዓኢሻ ጋር ሆነው ሳሉ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ቢን ሐቢብ ቢን አሰድ ቢን ዐብዲልዑዛ በዓኢሻ በኩል አለፈች። እኔም "ይህቺ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ናት። እርሷም ሌሊት እንደማትተኛ ገለፁልኝ።" አልኳቸው። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ሌሊት አትተኛም?! የምትችሉትን ስራ ያዙ። በአላህ እምላለሁ። (መስራት) እስክትሰለቹ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመስጠት) አይሰለችም።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 785]
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሐውላእ ቢንት ቱወይት - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነበረች። ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሲገቡ እርሷ ወጣች። ዓኢሻም እንዲህ አለቻቸው: ይህቺ ሴት ሌሊት አትተኛም። ይልቁንም ሌሊቱን በሙሉ የምታሳልፈው በሶላት ነው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በራሷ ላይ ማክበዷን በማውገዝ እንዲህ አሉ: ሌሊት አትተኛም?! ከመልካም ስራ መዘውተር የምትችሉትን ያህል ብቻ በመስራት ተጠመዱ። በአላህ እምላለሁ! አላህ ባሮቹ ስራን ከመስራት እስኪሰለቹ እና እስኪተዉ ድረስ ለደጋግና ታዛዥ ባሮቹ በአምልኳቸው፣ በመልካምና በጎ ስራዎቻቸው ምንዳና አጅር ከመስጠት አይሰለችም።