عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«قَالَ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى: أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ، مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ» قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ: اقْرَؤُوا إِنْ شِئْتُمْ: {فَلاَ تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُنٍ} [السجدة: 17].
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4779]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
«አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"» «አቡ ሁረይራም እንዲህ አለ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።} [አስሰጅዳ:17]"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4779]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን ተናገሩ: "ደጋግ ባሪያዎቼን ጀነት ውስጥ ለማላቅ ስለርሱ ምንነት አይን ያላየችውን፤ ስለርሱ ባህሪ ጆሮ ያልሰማችውን፤ ስለእውነተኛ ሁኔታዋ በሰው ቀልብ ላይ ውል ብሎ ያላለፈና ያልተከሰተን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።" አቡ ሁረይራም (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ:
{ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።}" [አስሰጅዳ:17]