የሐዲሦች ዝርዝር

በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።
عربي الإنجليزية الأوردية
በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።
عربي الإنجليزية الأوردية
በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።
عربي الإنجليزية الأوردية
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ።
عربي الإنجليزية الأوردية
አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም
عربي الإنجليزية الأوردية
የትንሳኤ ቀን አንድ ሰውዬ ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል። የሆዱ አንጀትም ይዘረገፋል። አህያ በወፍጮው እንደሚሽከረከረውም የተዘረገፈውን አንጀት ይዞ ይሽከረከራል።
عربي الإنجليزية الأوردية
ይህ ከሰባ አመት ጀምሮ እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ነው። እርሱም እሳት ውስጥ ወደ ጥልቀቷ መጨረሻ ዛሬ እስኪደርስ ድረስ እየተምዘገዘገ ነበር።" አሉ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ ይንፈቀፈቃል። ከርሱ የበለጠ ቅጣት የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም አያስብም። እርሱ እየተቀጣ ያለው ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት ነው።
عربي الإنجليزية الأوردية
(ለጀነት ነዋሪዎች) አንድ ተጣሪ ይጣራና "ለናንተ ጤና አላችሁ መቼም አትታመሙም፤ ለናንተ ህይወት አላችሁ መቼም አትሞቱም፤ ለናንተ ወጣትነት አላችሁ መቼም አታረጁም፤ ለናንተ በፀጋ ውስጥ መጣቀም አላችሁ መቼም አትቸገሩም።
عربي الإنجليزية الأوردية
አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ።
عربي الإنجليزية الأوردية
የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?
عربي الإنجليزية الأوردية
'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው።
عربي الإنجليزية الأوردية
እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል
عربي الإنجليزية الأوردية
የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።
عربي الإنجليزية الأوردية
በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። እንደዛሬ መልካምና መጥፎ ነገር ተመልክቼ አላውቅም። እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃቹ ብዙ ታለቅሱ ነበር።
عربي الإنجليزية الأوردية
ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።
عربي الإنجليزية الأوردية
ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች።
عربي الإنجليزية الأوردية
አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።
عربي الإنجليزية الأوردية
ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።
عربي الإنجليزية الأوردية
አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።
عربي الإنجليزية الأوردية
አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።
عربي الإنجليزية الأوردية
ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው።
عربي الإنجليزية الإندونيسية