+ -

عَنْ أُسَامَةَ بْنِ زَيْدٍ رضي الله عنه قَالَ: قِيلَ لَهُ: أَلَا تَدْخُلُ عَلَى عُثْمَانَ فَتُكَلِّمَهُ؟ فَقَالَ: أَتَرَوْنَ أَنِّي لَا أُكَلِّمُهُ إِلَّا أُسْمِعُكُمْ؟ وَاللهِ لَقَدْ كَلَّمْتُهُ فِيمَا بَيْنِي وَبَيْنَهُ، مَا دُونَ أَنْ أَفْتَتِحَ أَمْرًا لَا أُحِبُّ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ فَتَحَهُ، وَلَا أَقُولُ لِأَحَدٍ يَكُونُ عَلَيَّ أَمِيرًا: إِنَّهُ خَيْرُ النَّاسِ بَعْدَمَا سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«يُؤْتَى بِالرَّجُلِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، فَيُلْقَى فِي النَّارِ، فَتَنْدَلِقُ أَقْتَابُ بَطْنِهِ، فَيَدُورُ بِهَا كَمَا يَدُورُ الْحِمَارُ بِالرَّحَى، فَيَجْتَمِعُ إِلَيْهِ أَهْلُ النَّارِ، فَيَقُولُونَ: يَا فُلَانُ مَا لَكَ؟ أَلَمْ تَكُنْ تَأْمُرُ بِالْمَعْرُوفِ، وَتَنْهَى عَنِ الْمُنْكَرِ؟ فَيَقُولُ: بَلَى، قَدْ كُنْتُ آمُرُ بِالْمَعْرُوفِ وَلَا آتِيهِ، وَأَنْهَى عَنِ الْمُنْكَرِ وَآتِيهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2989]
المزيــد ...

ከኡሳማ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉት: «ዑሥማን ዘንድ ገብተህ አታናግረውምን?» ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም አላቸው: «እናንተ በምትሰሙበት መልኩ ካልሆነ በቀር የማላናግረው ይመስላችኋልን? በአላህ እምላለሁ (መሪን በግልፅ የመቃወምን በር) ሳልከፍት በኔና በርሱ መካከል ማንም ሳይኖር አናግሬዋለሁ። የመጀመሪያው የፊትና በር ከፋች መሆንንም አልወድም። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህን ሲሉ ከሰማሁ በኋላ በኔ ላይ ለተሾመ ለአንዱም (ለማስመሰል ብዬ) ከሰዎች ሁሉ ምርጡ ነው አልልም:
"የትንሳኤ ቀን አንድ ሰውዬ ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል። የሆዱ አንጀትም ይዘረገፋል። አህያ በወፍጮው እንደሚሽከረከረውም የተዘረገፈውን አንጀት ይዞ ይሽከረከራል። የእሳት ሰዎችም ወደርሱ ይሰበሰቡና እንዲህ ይሉታል: ‹እከሌ ሆይ! ምን አገኘህ? በመልካም ታዝ ከመጥፎ ትከለክል አልነበረምን?› እርሱም: ‹እንዴታ! በመልካም አዝዝና አልሰራውም ነበር፤ ከመጥፎም እከለክልና እሰራው ነበር።› ይላቸዋል።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2989]

ትንታኔ

ለኡሳማ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ተባሉ: ዑሥማን ቢን ዐፋን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ ገብተህ በሰዎች መካከል ስለተከሰተው ፈተናና ከመሰረቱ ፈተናውን በማጥፋት ላይ እንዲለፋ አታናግራቸውምን? እርሱም: ፈተናን ላለማባባስ ማስተካከልን በመፈለግ በድብቅ እንዳናገረው፤ መሪዎችን በይፋ ማውገዝንና በኸሊፋው ላይ የመንጠራራት ሰበብ መሆን እንደማይፈልግ ነገራቸው። ይህን ማድረግ የፈተናና የመጥፎ በር በመሆኑ ለዚህ በር የመጀመሪያው ከፋች መሆን እንደማይፈልግም ነገራቸው።
ቀጥሎ ኡሳማ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - : እርሱ መሪዎችን በድብቅ እንደሚመክርና ከየትኛውም መሪ ጋር ቢሆን እንኳ እንደማይቅለሰለስና በፊትለፊታቸውም ጥፋታቸውን እንደማያሞግሳቸው ተናገረ። ይህንንም የሚያደርገው ይህንን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰማ በኋላ ነው:- የትንሳኤ ቀን አንድ ሰው ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል። ከቅጣቱ ሀይለኝነትና ከሀሩሩ አደገኝነት የተነሳም አንጀቱ ከሆዱ በፍጥነት ወጥቶ ይዘረገፋል። በዚህም ሁኔታ አህያ በወፍጮው (የድንጋይ መፍጫ) ዙሪያ እየዞረ እንደሚኖረው እሳት ውስጥ አንጀቱን ይዞ ይሽከረከራል። በዙሪያውም የእሳት ሰዎች በመክበብ ይሰበሰቡና "እከሌ ሆይ! በመልካም የምታዘን ከመጥፎ የምትከለክለን አልነበርክምን?" በማለት ይጠይቁታል።
እርሱም: እኔ በመልካም የማዝና የማልፈፅመው ከመጥፎ የምከለክልና የምሰራው ሰው ነበርኩ ይላል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመሰረቱ መሪዎችን መምከር በነርሱና በርሱ መካከል ብቻ ተሁኖ ፤ በሰዎች መካከልም ወሬውን ሳያዛምቱ ነው።
  2. ንግግሩ ከድርጊቱ ጋር የሚቃረን ሰው ላይ ብርቱ ዛቻ መቅረቡን እንረዳለን።
  3. ከመሪዎች ጋር አደብ መላበስና ለነርሱም ቢሆን ርህራሄ እንደሚገባቸው፤ እነርሱንም በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. እውነት በሆነ ጉዳይ ከመሪዎች ጋር መቅለስለስና ውስጡ ከሚያምንበት በተቃራኒ ግልፅ ማድረግ (በውሸት እንደሚያሞግስ ሰው ይመስል) መወገዙን እንረዳለን።