عن ابن مسعود رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم:
«الْجَنَّةُ أَقْرَبُ إِلَى أَحَدِكُمْ مِنْ شِرَاكِ نَعْلِهِ، وَالنَّارُ مِثْلُ ذَلِكَ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6488]
المزيــد ...
ኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6488]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሰው ልጅ ጀነትም ይሁን ጀሀነም በእግሩ ላይ እንዳለው የጫማው ማሰሪያ ቅርብ መሆናቸውን ተናገሩ። ምክንያቱም (ሳያስበው) አሏህን የሚያስደስት የሆነን መልካም ስራ ይሰራና በዛ ሰበብ ጀነት ይገባል። ወይም መጥፎ ስራ ይሰራና ጀሀነም ለመግባት ሰበብ ይሆንበታል።