+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الدُّنْيَا سِجْنُ الْمُؤْمِنِ وَجَنَّةُ الْكَافِرِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2956]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"ዱንያ ለአማኞች እስር ቤት ለከሃዲዎች ጀነት ናት።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2956]

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አማኝ የሆነ ሰው በዱንያ ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላን በመራቅ በኩል ሸሪዓዊ በሆኑ ሃላፊነቶች ስለታሰረ የዱንያ ህይወት ለአማኝ እስር ቤት እንደሆነች እና ከዚህም ሲሞት አላህ ለርሱ ወዳዘጋጀለት ዘውታሪ ፀጋ ተሸጋግሮ እንደሚያርፍ ተናገሩ። ከሃዲ የሆነ ሰው ደግሞ ነፍሱ የፈለገችውን ሁሉና ዝንባሌው የመራውን ሁሉ ስለሚሰራ ዱንያ ለከሃዲ ጀነት መሆኗንና ሲሞትም አላህ የትንሳኤ ቀን ወዳዘጋጀለት ዘውታሪ ቅጣት ይሸጋገራል ብለው ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ሁሉም አማኝ ዱንያ ውስጥ ከሚገኙ ክልክልና የተጠሉ ከሆኑ ስሜቶች የታሰረና የተከለከለ ነው። ከባባድ ትእዛዛትን በመፈፀምም የተገደደ ነው። ሲሞት ከዚህ እረፍት በማግኘት አላህ ወዳዘጋጀለት ዘውታሪ ፀጋና ከጉድለት ወደፀዳ ተድላ ይሸጋገራል። ከሃዲ ግን ዱንያ ውስጥ ለርሱ ከማነሷና በመከራ ከመደፍረሷም ጋር የተወሰነ ያገኘው የዱንያ ዕጣ ፈንታ አለው። ሲሞትም ወደ ዘውታሪ ቅጣትና ዘላለማዊ ዕድለ ቢስነት ይገባል።"
  2. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ለአማኝ እስር ቤት ናት) ሲሉ ምድር ላይ በፀጋ ቢኖር እንኳ ጀነት ውስጥ ያለው ፀጋ ምድር ላይ ካገኘው የተሻለ ነው (ከጀነት አንፃር የዱኒያ ፀጋ እንደእስር ቤት ነው) ማለት ነው። (ለከሃዲ ጀነት ናት) ማለት ደግሞ ምድር ላይ በመከራ ቢያሳልፍ እንኳ የጀሀነም እሳት ምድር ላይ ካየው መከራ የባሰ የከፋ ነው (የዱኒያ ሰቆቃ ከጀሀነም አንፃር ለካፊር እንደ ጀነት ነው) ማለት ነው።"
  3. ዱንያ አላህ ዘንድ የወረደች መሆኗን እንረዳለን።
  4. ዱንያ ለአማኞች የፈተናና የሙከራ ሃገር መሆኗን እንረዳለን።
  5. ከሃዲ ጀነቱን ዱንያ ውስጥ አቻኩሎታል። ስለዚህም በመጪው አለም ጀነትና ፀጋዎቿን በመነፈግ ይቀጣል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الصربية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ