عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ مِنَ اللَّهِ، وَالحُلُمُ مِنَ الشَّيْطَانِ، فَإِذَا حَلَمَ أَحَدُكُمْ حُلُمًا يَخَافُهُ فَلْيَبْصُقْ عَنْ يَسَارِهِ، وَلْيَتَعَوَّذْ بِاللَّهِ مِنْ شَرِّهَا، فَإِنَّهَا لاَ تَضُرُّهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3292]
المزيــد ...
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"መልካም ህልም ከአላህ ነው። መጥፎ ህልም ከሸይጧን ነው። አንዳችሁ የሚፈራውን መጥፎ ህልም የተመለከተ ጊዜ ወደ ግራው ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ያኔ እርሷም አትጎዳውም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3292]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በእንቅልፍ የሚያስደስት መልካም ህልም መመልከት ከአላህ እንደሆነና የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ቅብዥር መመልከት ደግሞ ከሸይጧን እንደሆነ ተናገሩ።
የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ሰው ወደ ግራው አቅጣጫ ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ቅብዥሩን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂዎች ሰላም ለመሆን የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው እርሷ አትጎዳውም።