عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
جَاءَ رَجُلٌ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: السَّلَامُ عَلَيْكُمْ، فَرَدَّ عَلَيْهِ ثُمَّ جَلَسَ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «عَشْرٌ» ثُمَّ جَاءَ آخَرُ فَقَالَ: السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ، فَرَدَّ عَلَيْهِ فَجَلَسَ، فَقَالَ: «عِشْرُونَ» ثُمَّ جَاءَ آخَرُ فَقَالَ: السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ، فَرَدَّ عَلَيْهِ فَجَلَسَ، فَقَالَ: «ثَلَاثُونَ».
[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد والدارمي] - [سنن أبي داود: 5195]
المزيــد ...
ከዒምራን ቢን ሑሶይን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሀያ" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሰላሳ" አሉ።»
[ሐሰን ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 5195]
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት (አስሰላሙ ዐለይኩም) አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ አስር ምንዳ ተጽፎለታል አሉ። ከዚያም ሌላ ሰው መጣና (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ) አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ ሀያ ምንዳ አለው አሉ። ከዚያም ሌላ ሰውዬ መጣና (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ) አላቸው። ሰላምታውን መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ ሰላሳ ምንዳ አለው አሉ። ማለትም እያንዳንዱ ቃል አስር ምንዳ ያስገኛል ማለታቸው ነው።