عَنْ سُلَيْمَانَ بْنِ صُرَدٍ رضي الله عنه قَالَ:
كُنْتُ جَالِسًا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَرَجُلاَنِ يَسْتَبَّانِ، فَأَحَدُهُمَا احْمَرَّ وَجْهُهُ، وَانْتَفَخَتْ أَوْدَاجُهُ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنِّي لَأَعْلَمُ كَلِمَةً لَوْ قَالَهَا ذَهَبَ عَنْهُ مَا يَجِدُ، لَوْ قَالَ: أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ، ذَهَبَ عَنْهُ مَا يَجِدُ» فَقَالُوا لَهُ: إِنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «تَعَوَّذْ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ»، فَقَالَ: وَهَلْ بِي جُنُونٌ؟
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3282]
المزيــد ...
ከሱለይማን ቢን ሱረድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ተቀምጬ ሳለ ሁለት ሰዎች ይሰዳደባሉ። አንዱ ፊቱ ቀልቷል፣ ደም ስሩ ተገታትሯል። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ "እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።" ለርሱም ሄደው "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ" እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም "እኔ ላይ እብደት አለብኝ እንዴ?" አላቸው።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3282]
ሁለት ሰዎች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፊት ተሰዳደቡ። የአንደኛቸው ፊት ቀላ፣ አንገቱ ዘንድ ያሉት ደምስሮቹም ተገታተሩ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "እኔ አንዲትን ንግግር አውቃለሁ ይህ የተናደደ ሰው ቃሏን ቢናገራት ቁጣው ከርሱ ይወገድለት ነበር። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧኒ ረጂም ቢል ይወገድለት ነበር።"
ለርሱም "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ እያሉህ ነው።" አሉት።
እርሱም እብደት ያለበት ሰው ካልሆነ በቀር ከሸይጧን የማይጠበቅ መስሎት "እኔ እብድ ነኝ እንዴ?" አላቸው።