عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَلاَ أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ؟» قَالُوا: بَلَى. قَالَ: «ذِكْرُ اللهِ تَعَالَى».
[صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 3377]
المزيــد ...
ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣ ለናንተ ወርቅና ብር ከመመፅወት የሚበልጥላችሁን ስራ፣ ጠላቶቻችሁን ተገናኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱበት አንገታችሁን ከሚመቱበት ስራችሁም በላጩ የሆነውን ስራ አልነግራችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "አላህን ማውሳት ነው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3377]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት ጠየቁ :
ልዕለ ኃያሉ ንጉሱ አላህ ዘንድ በላጩን፣ የላቀውን፣ የፋፋውን፣ የፀዳውንና የጠራውን ስራችሁን እንድነግራችሁ ትፈልጋላችሁን? ?
ጀነት ውስጥም ያለውን ደረጃችሁንም ከፍ የሚያደርግላችሁን ስራ?
ወርቅና ብር ከመመፅወትም ለናንተ የሚበልጥላችሁን?
ከከሀዲያን ጋር ለውጊያ ተገናኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትቀሉና አንገቶቻችሁንም ከሚቀሉ የሚበልጠውን?
ሶሐቦችም: አዎ ይህንን እንፈልጋለን አሉ።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ወቅትና በአጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ አላህን ማውሳት ነው አሏቸው።