+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«أَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى مَا يَمْحُو اللهُ بِهِ الْخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟» قَالُوا بَلَى يَا رَسُولَ اللهِ قَالَ: «إِسْبَاغُ الْوُضُوءِ عَلَى الْمَكَارِهِ، وَكَثْرَةُ الْخُطَا إِلَى الْمَسَاجِدِ، وَانْتِظَارُ الصَّلَاةِ بَعْدَ الصَّلَاةِ، فَذَلِكُمُ الرِّبَاطُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 251]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ" አሉ። እርሳቸውም "በአስቸጋሪ ወቅት ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጂድ እርምጃ ማብዛት፣ አንድ ሰላት ካለቀ በኋላ ሌላኛው ሶላት መጠበቅ፤ ይሀው ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ) ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 251]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለወንጀሎቻቸው መማር፣ ከጠባቂ መላዕክት መዝገብ ወንጀላቸውን ለማሰረዝ፣ በጀነት ውስጥም ደረጃዎችን ከፍ ለማድረግ ምክንያት የሚሆኑ ስራዎችን እንዲጠቁሟቸው ይፈልጉ እንደሆነ ባልደረቦቻቸውን ጠየቋቸው።
ሶሐቦችም: "አዎን እንፈልጋለን" አሉ። እሳቸውም እንዲህ አሉ:
የመጀመሪያው: እንደ ቅዝቃዜ፣ የውሃ ማነስ፣ የሰውነት ህመምና አቃጣይ ውሃን የመሰሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ዉዱእን መሙላትና ማዳረስ ነው።
ሁለተኛው: እርምጃን ከሩቅ አካባቢ ወደ መስጂድ ማብዛትና ደጋግሞ መመላለስ ነው።
ሶስተኛ: የሶላትን ወቅት መጠበቅ፣ ልብን በሶላት ማንጠልጠል፣ ለሶላት መዘጋጀት፣ ጀመዓን ለመጠበቅ መስጂድ ውስጥ ለሶላት መቀመጥ፣ ከሰገደም በኋላ ለሌላ ሶላት መስገጃው ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ነው።
ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህ ጉዳዮች ትክክለኛው ዘብ መጠበቅ እንደሆኑ ገለፁ። ምክንያቱም የሰይጣንን መንገዶች በነፍስ ላይ ስለምትዘጋ፣ ስሜትን ስለምታሸንፍ፣ ነፍስ ለወስዋስ ተገዥ እንዳትሆን ስለምትከለክል ነው። ነፍስን በማሸነፍ የአላህ ጭፍራ የሰይጣንን ሰራዊት ያሸንፉበታል። ትልቁ ጂሀድም ይህ ነው። ስለዚህ ይህ ድንበር ኬላ ላይ ጠላትን በመጠበቅ ደረጃ እንደሆነ አድርገው ገለፁት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መስጂድ ውስጥ የህብረት ሶላትን የመጠባበቅ አንገብጋቢነቱን፤ ለሶላት ትኩረት መስጠትና ከሶላት በሌላ ነገር መጠመድ እንደሌለብንም እንረዳለን።
  2. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስራው የሚያስገኘውን ትልቅ ምንዳ በጥያቄያዊ መንገድ አስቀድመው ባልደረቦቻቸውን በማጓጓታቸው የትምህርት አቀራረባቸውን ማማር እንረዳለን። ይህም አንዱ የማስተማሪያ መንገድ ነው።
  3. አንድን ጉዳይ በጥያቄና መልስ መንገድ ማቅረብ ብይኑን መጀመሪያ በመደበቅና ቀጥሎ በማብራራት ንግግሩ ነፍስ ውስጥ እንዲቀር የማድረግ ጥቅም አለው።
  4. ነወዊ አላህ ይዘንላቸውና «ይህ ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ)» ማለት ተፈላጊው ዘብ መጠበቅ ይህ ነው ማለት ነው። ሪባጥ የሚለው ቃል መሰረት በአንድ ነገር ላይ መታጠር ማለት ሲሆን በነዚህ ስራዎች አላህን በመገዛት ላይ ነፍሱን ስለሚያጥር ነው። "ጂሃድ ማለት ነፍስን መታገል ነው።" እንደሚባለው በላጩ ሪባጥ ይህ ነውም ተብሏል። በሌላ አባባል ደሞ ቀላሉና የሚመቸው ሪባጥ ነው ማለት ተፈልጎበት ሊሆንም ያስመቻል። ማለትም ከሪባጥ አይነቶች አንዱ ነው እንደማለት ነው።
  5. (አል) የምትለዋ ገላጭ ገብታ "አር‐ሪባጥ" የምትለዋ ቃል መደጋገሟ የነዚህ ስራዎችን ትልቅነት ያስረዳናል።