عَنْ حَارِثَةَ بْنِ وَهْبٍ الخُزَاعِيِّ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِأَهْلِ الجَنَّةِ؟ كُلُّ ضَعِيفٍ مُتَضَعِّفٍ، لَوْ أَقْسَمَ عَلَى اللَّهِ لَأَبَرَّهُ، أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِأَهْلِ النَّارِ: كُلُّ عُتُلٍّ جَوَّاظٍ مُسْتَكْبِرٍ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4918]
المزيــد ...
ከሓሪሣ ቢን ወህብ አልኹዛዒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"የጀነት ነዋሪ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ደካማ፣ ዝቅ የሚደረግ፣ በአላህ ላይ ቢምል ግን አላህ መሃላውን እውን የሚያደርግለት የሆነ ሁሉ ነው። የእሳት ነዋሪስ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ልበ ደረቅ፣ ትዕቢተኛና በኩራት የተሞላ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4918]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነትና የእሳት ነዋሪዎችን አንዳንድ ባህሪያት ተናገሩ።
አብዛኛው የጀነት ነዋሪዎች "ደካማና ዝቅ የሚደረጉ ናቸው።" ማለትም ለአላህ የሚተናነስና የሚዋደቅ፣ ነፍሱንም ለአላህ ዝቅ ያደረገ ነው። አንዳንድ ሰዎች ዝቅ ያደርጉታልም ይንቁታልም። ይህ ለአላህ ብሎ ነፍሱን ዝቅ ያደረገ ሰው የአላህን ችሮታ ፈልጎ በአንድ ጉዳይ በአላህ ላይ ቢምል አላህ መሀላውን እውን የሚያደርግለት፤ የማለበትን ነገር የሚፈፅምለት፤ ፍላጎቱንና ዱዓውን የሚያሟላለት አይነት ሰው ነው።
አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች "ልበ ደረቅ የሆነ ሁሉ" ይህ ቃል ደረቅ ለሆነ፣ አክርሮ ለሚሟገት ወይም መልካምን ለማይቀበል ባለጌ ሰው የሚውል ነው። "ትዕቢተኛ" (ጀዋዝ) ይህም ማለት ኩራተኛ፣ ሆዳም፣ ዝርፍጥ፣ ሲራመድ የሚንቦጣረርና መጥፎ ስነምግባር የተላበሰ ማለት ነው። "በኩራት የተሞላ" ማለት እውነትን ባለመቀበልና ሌላውን በመናቅ የሚኮራ ማለት ነው።