عن جابر رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«أَفْضَلُ الذِّكْرِ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَفْضَلُ الدُّعَاءِ: الْحَمْدُ لِلهِ».

[حسن] - [رواه الترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه]
المزيــد ...

ጃቢር ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡
"በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሓምዱሊላህ' ማለት ነው።'"

Hasan/Sound. - [Ibn Maajah]

ትንታኔ

ነቢዩ ﷺ በላጩ ዚክር "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" - ትርጉሙም፡ ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው የለም - መሆኑን፤ ከዱዓእ በላጩ ደግሞ "አልሓምዱሊላህ" - ትርጉሙም፡ ፀጋንም የሚውለው ለተሟላ ውብ መገለጫም የተገባው እርሱ አላህ ብቻ መሆኑን ማመን - እንደሆነ ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አሏህን በተውሒድ ቃል ማስታወስና በምስጋና ቃል መማፀን ማብዛት መበረታታቱን እንረዳለን።