+ -

عَنْ عَائِشَةَ رضي الله عنها قَالَتْ:
فَقَدْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لَيْلَةً مِنَ الْفِرَاشِ فَالْتَمَسْتُهُ فَوَقَعَتْ يَدِي عَلَى بَطْنِ قَدَمَيْهِ وَهُوَ فِي الْمَسْجِدِ وَهُمَا مَنْصُوبَتَانِ، وَهُوَ يَقُولُ: «اللهُمَّ أَعُوذُ بِرِضَاكَ مِنْ سَخَطِكَ، وَبِمُعَافَاتِكَ مِنْ عُقُوبَتِكَ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْكَ لَا أُحْصِي ثَنَاءً عَلَيْكَ أَنْتَ كَمَا أَثْنَيْتَ عَلَى نَفْسِكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 486]
المزيــد ...

ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦
«በአንድ ምሽት የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከፍራሼ ላይ አጣኋቸው። በዳሰሳ ስፈልጋቸውም እጄ መስገጃቸው ላይ የተተከለችው የእግራቸው ውስጥ ላይ አረፈች። እርሳቸውም እንዲህ እያሉ ነበር " አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 486]

ትንታኔ

ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ አለች "ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጎን ተኝቼ ነበር። ሌሊት ላይ አጣኋቸሁ። ቤት ውስጥ ይሰግዱበት የነበረውን ስፍራ በእጄ ዳሰስኩ። በዛን ጊዜም ሱጁድ ላይ ተደፍተው እግራቸውን ተተክለው አገኘሁ። እርሳቸውም እንዲህ እያሉ ነበር:
(በውዴታህ) በኔ ላይም ይሁን በኡመቴ ላይ ከምትቆጣው (ቁጣህ) (እጠበቃለሁ) እቃረባለሁ። (ከቅጣትህ) ይቅር ባይነትህ ብዙ ነውና (በይቅር ባይነትህ) (እጠበቃለሁ)(በአንተ ከአንተ እጠበቃለሁ።) ውብ በሆኑት ባህሪያትህ የልቅና መገለጫ ከሆኑት ባህሪያትህ እጠበቃለሁ። ከአንተ በቀር ከአንተ ለሚመጣው ቅጣት የሚጠብቅ የለምና። ወደ አላህ በመጠጋት ካልሆነ በቀርም ከአላህ መዳኛም መጠጊያም የለም። (በአንተ ላይ አወድሼ አልዘልቅም።) ፀጋህንና በጎ ውለታህን ቆጥሬ መዝለቅ ስለማልችል አንተ የሚገባህንም ውዳሴ በቁጥርም በገደብም ማወደሱን ብጥር እንኳ አልችልም። ለራስህ የሚገባውን በቂ ውዳሴ በራስህ ላይ ያወደስከው አንተ ብቻ ነህና (አንተ ነፍስህን ባወደስክበት ልክ ማወደስ አልችልም።) አንተን የማወደስ ሐቁን በአግባቡ መወጣት የሚችልስ ሌላ አካል ማን አለና?!

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሱጁድ ላይ ይሄን ዱዓ ማለት ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  2. ሚረክ እንዲህ ብለዋል: «በአንድ የነሳኢ ዘገባ ደሞ ይህን ዱዓ ሶላታቸውን አጠናቀው ወደ መኝታቸው ሲወጡ እንደሚሉት ተዘግቧል።»
  3. አላህን በቁርአንና ሐዲሥ በመጡ ባህርያቱ ማወደስና በስሞቹ ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  4. ይህ ሐዲሥ ፈጣሪን ሩኩዕና ሱጁድ ውስጥ ማላቅ እንደሚገባ ያስረዳናል።
  5. በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ዛት መጠበቅ እንደሚፈቀደው በአላህ ባህሪም መጠበቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  6. ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ንግግር ውስጥ ረቂቅ ሀሳብ ይገኛል። እርሱም: እርሳቸው ከአላህ ቁጣ በውዴታው፣ ከቅጣቱ ደሞ በይቅርታው ተጠበቁ። ውዴታና ቁጣ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ናቸው። እንዲሁም ይቅር ባይነትና በወንጀል መቅጣትም ተቃራኒ ናቸው። ለርሱ ተነፃፃሪ የሌለውን አላህን ሱብሓነሁ ወተዓላ ሲጠቅሱ ግን ከርሱ በሌላ ሳይሆን በራሱ ተጠበቁ። የዚህም ሀሳብ: ይቅር ባይነቱ የተጠየቀው አላህ ሊመለክና ሊወደስበት ከሚገባው መብቱ ስለማጓደላችን ነው። (በአንተ ላይ አወድሼ አልዘልቅም።) ሲሉ አንተን በሚገባህ ልክ ማወደስ የምችልበት አቅሙ የለኝም ማለታቸው ነው።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ