عَنْ أُبَيِّ بْنِ كَعْبٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
كَانَ رَجُلٌ لَا أَعْلَمُ رَجُلًا أَبْعَدَ مِنَ الْمَسْجِدِ مِنْهُ، وَكَانَ لَا تُخْطِئُهُ صَلَاةٌ، قَالَ: فَقِيلَ لَهُ: أَوْ قُلْتُ لَهُ: لَوْ اشْتَرَيْتَ حِمَارًا تَرْكَبُهُ فِي الظَّلْمَاءِ، وَفِي الرَّمْضَاءِ، قَالَ: مَا يَسُرُّنِي أَنَّ مَنْزِلِي إِلَى جَنْبِ الْمَسْجِدِ، إِنِّي أُرِيدُ أَنْ يُكْتَبَ لِي مَمْشَايَ إِلَى الْمَسْجِدِ، وَرُجُوعِي إِذَا رَجَعْتُ إِلَى أَهْلِي، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «قَدْ جَمَعَ اللهُ لَكَ ذَلِكَ كُلَّهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 663]
المزيــد ...
ከኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«አንድ ሰውዬ ነበር። ከርሱ የበለጠ ቤቱ ከመስጂድ የራቀ አንድም ሰው አላውቅም። ሆኖም አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ለርሱም እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበለት ‐ ወይም እንዲህ ብየ ጠየቅኩት ‐ : "እንደው በጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም?" እርሱም "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። የአላህም መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።" አሉት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 663]
ኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተናገሩት: "አንድ ቤቱ ከመስጂደ ነበዊይ እጅግ የራቀ ከአንሷር የሆነ ሰውዬ ነበር። አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ይልቁኑም ሁሉንም ሶላት ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተገኝቶ ይሰግድ ነበር። ለርሱም እንዲህ ተባለ: እንደው በምሽቱ ጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም? እርሱም እንዲህ አለ: "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። ንግግሩም ነቢዩ ዘንድ ደረሰ። እርሳቸውም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።"