عَنِ ‌ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما:
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَطَبَ النَّاسَ يَوْمَ فَتْحِ مَكَّةَ، فَقَالَ: «يَا أَيُّهَا النَّاسُ، إِنَّ اللهَ قَدْ أَذْهَبَ عَنْكُمْ عُبِّيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ وَتَعَاظُمَهَا بِآبَائِهَا، فَالنَّاسُ رَجُلَانِ: بَرٌّ تَقِيٌّ كَرِيمٌ عَلَى اللهِ، وَفَاجِرٌ شَقِيٌّ هَيِّنٌ عَلَى اللهِ، وَالنَّاسُ بَنُو آدَمَ، وَخَلَقَ اللهُ آدَمَ مِنْ تُرَابٍ، قَالَ اللهُ: {يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ ذَكَرٍ وَأُنْثَى وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِنْدَ اللهِ أَتْقَاكُمْ إِنَّ اللهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ} [الحجرات: 13]».

[صحيح] - [رواه الترمذي وابن حبان]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ እለት ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ ' እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል። ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው። በጎ፣ አላህን ፈሪና አላህ ዘንድ የተከበረ፤ አመፀኛ፣ ጠማማና አላህ ዘንድ የወረደ ናቸው። ሰዎች የአደም ልጆች ናቸው። አላህም አደምን ከአፈር ነው የፈጠረው። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ። አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልፅን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።} [ሑጁራት: 13]'"

Sahih/Authentic. - [At-Tirmidhi]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ እለት ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርናን ዘመን ኩራት፣ ትዕቢትንና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል። ሰዎች ሁለት አይነት ብቻ ናቸው።
ወይ አማኝ፣ በጎ፣ አላህን ፈሪና ለአላህ ባሪያ የሆነ ነው። ይህ ግለሰብ ሰዎች ዘንድ የተከበረ ዘርና ጎሳ ባለቤት ባይሆን እንኳ አላህ ዘንድ የተከበረ ነው።
ወይም ደግሞ ከሀዲ፣ አመፀኛና ጠማማ ነው። ይህም ስልጣንና ክብር ያለው ከተከበረ ዘር እንኳ ቢሆን አላህ ዘንድ ከምንም ነገር ጋር የማይስተካከል የተዋረደና የዘቀጠ ነው።
ሰዎች ሁሉ የኣደም ልጆች ናቸው። አላህም ኣደምን ከአፈር ነው የፈጠራቸው። መሰረቱ ከአፈር የሆነ ደግሞ በራሱ ሊኮራና ሊደነቅ አይገባውም። የዚህም ማረጋገጫ እንዲህ የሚለው የአላህ ንግግር ነው፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ። አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልፅን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።} [ሑጁራት: 13

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በዘርና በጎሳ መኩራራት መከልከሉን እንረዳለን።