+ -

عَنْ ‌الزُّبَيْرِ بْنِ الْعَوَّامِ قَالَ:
لَمَّا نَزَلَتْ: {ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ} [التكاثر: 8]، قَالَ الزُّبَيْرُ: يَا رَسُولَ اللهِ، وَأَيُّ النَّعِيمِ نُسْأَلُ عَنْهُ، وَإِنَّمَا هُمَا الْأَسْوَدَانِ التَّمْرُ وَالْمَاءُ؟ قَالَ: «أَمَا إِنَّهُ سَيَكُونُ».

[حسن] - [رواه الترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 3356]
المزيــد ...

ከዙበይር ቢን አልዓዋም እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል:
{ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} [አትተካሡር: 8] የሚለው አንቀፅ የወረደ ጊዜ ዙበይር እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንመገብ የነበረው ሁለቱን ጥቁሮች ተምርና ውሃ ነው። ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው?" እሳቸውም "እርሱኑ ሳይሆን አይቀርም የምትጠየቁት።" አሉት።

[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3356]

ትንታኔ

ተከታዩ አንቀፅ በወረደ ጊዜ: {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} ማለትም አላህ በናንተ ላይ ለዋለላችሁ ፀጋ ማመስገናችሁን የምትጠየቁ ናችሁ። ዙበይር ቢን አልዓዋም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው? እነዚህ ሁለት ፀጋዎች ለመጠየቅ የሚያነሳሱ አይደሉም'ኮ እነርሱም ተምርና ውሃ ናቸው።"
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እናንተ በዚህ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ከመሆናችሁም ጋር ስለነዚህ ፀጋዎች ትጠየቃላችሁ። እነዚህ ሁለቱም ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎቹ መካከል ናቸውና።" አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በፀጋዎች ላይ አላህን ማመስገን እንደሚገባ ጠንከር ባለ መልኩ መምጣቱን እንረዳለን።
  2. ትንሽም ይሁን ብዙ ፀጋ የትኛውም ባሪያ የትንሳኤ ቀን ስለርሱ የሚጠየቅበት መሆኑን እንረዳለን።
ተጨማሪ