+ -

عَنْ ‌أَبِي هُرَيْرَةَ عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ:
«سَيَكُونُ فِي آخِرِ أُمَّتِي أُنَاسٌ يُحَدِّثُونَكُمْ مَا لَمْ تَسْمَعُوا أَنْتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ، فَإِيَّاكُمْ وَإِيَّاهُمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 6]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"በመጨረሻዎቹ ሕዝቦቼ (ኡመቴ) ውስጥ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ያልሰማችሁትን የሚነግሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ። አደራችሁን አደራችሁን ተጠንቀቋቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 6]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመጨረሻዎቹ ኡመታቸው ውስጥ ውሸትን የሚቀጥፉ ሰዎች ብቅ እንደሚሉ ተናገሩ። ከነርሱ በፊት አንድም ሰው ያልተናገረውን ይናገራሉ፤ የተዋሹና የተቀጠፉ ሐዲሦችን ይናገራሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነርሱ እንድንርቅና እንዳንቀማመጣቸው፣ ከርሱ መራቅ እስኪያቅተን ድረስ ይህ የተቀጠፈ (የተፈበረከ) ሐዲሥ ነፍስ ውስጥ ተፅዕኖ እንዳያሳድርብንም ሐዲሣቸውን አለመስማትን አዘዙን።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከነቢይነት ምልክቶች አንዱ ምልክት አለ። ይኸውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ውስጥ ለወደፊት የሚከሰትን ተናገሩ እንዳሉትም መከሰቱ ነው።
  2. በአላህ መልዕክተኛ ላይ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲሁም በኢስላም ላይ የሚዋሽን ሰው መራቅና ውሸታቸውን አለመስማት እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. ቅቡልነቱንና ትክክለኛነቱን እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ እንጂ ሐዲሦችን ከመቀበልም ከማሰራጨትም መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።