+ -

عن العِرْباضِ بن ساريةَ رضي الله عنه قال:
قام فينا رسول الله صلى الله عليه وسلم ذات يوم، فوَعَظَنا مَوعظةً بليغةً وَجِلتْ منها القلوبُ، وذَرَفتْ منها العيونُ، فقيل: يا رسول الله، وعظتَنَا موعظةَ مُودِّعٍ فاعهد إلينا بعهد. فقال: «عليكم بتقوى الله، والسمع والطاعة، وإن عبدًا حبشيًّا، وسترون من بعدي اختلافًا شديدًا، فعليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين، عَضُّوا عليها بالنواجِذ، وإياكم والأمور المحدثات، فإن كل بدعة ضلالة».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن ابن ماجه: 42]
المزيــد ...

ከዒርባድ ቢን ሳሪያህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁ) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 42]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦችን ልቦች በርሷ ምክንያት የራዱበትና ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰ ምክር መከሩ። ሰሐቦችም የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምክራቸው ጥግ የደረሰ መሆኑን ስላዩ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት የተሰናባች ምክር ትመስላለች።" በማለት ከርሳቸው ህልፈት በኋላ አጥብቀው የሚይዙትን አደራ ጠየቁ። እርሳቸውም "አላህን በመፍራት አደራ እላቹኃለሁ።" አሉ። ይህም ግዴታዎችን በመፈፀምና ክልክሎችን በመተው ነው። "ባሪያ በናንተ ላይ ቢሾም ወይም መሪ ሆኖ ቢመጣባችሁ እንኳ ለመሪዎች መስማትና መታዘዝን አደራ እላችኃለሁ።" ማለትም በናንተ ላይ ደረጃው የወረደ (አርጋችሁ የምታስቡት) ፍጡር መሪ ቢሆን እንኳ ፈተና ይቀጣጠላል ተብሎ ስለሚሰጋ በዚህ ላይ እምቢተኛ አትሁኑ ታዘዙት ማለት ነው። "እነሆ ከናንተ መካከል የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ያያል።" ቀጥለውም ከዚህ ልዩነት መውጫውን ገለፁላቸው። እሱም የርሳቸውን ሱና(ፈለግ) እና ከርሳቸው በኋላ የተመሩ የሆኑት ቅን ምትኮቻቸውን ሱና አጥብቆ በመያዝ ነው። እነሱም: አቡ በከር አስሲዲቅ፣ ዑመር ቢን አልኸጧብ፣ ዑሥማን ቢን ዐፋንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ የሁሉንም መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው። አጥብቃችሁ የምትይዙትም በማኘኪያ ጥርስ ነክሶ እንደመያዝ ነው። በዚህም ለማለት የፈለጉት ሱናን በመያዝና በማጥበቅ ላይ መጠንከርን ለመጠቆም ነው። በሃይማኖት ውስጥ ከተፈበረኩ አዳዲስ መጤ ጉዳዮችም አስጠነቀቋቸው። ሁሉም አዲስ መጤ ነገር ጥመት ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሱናን አጥብቆ መያዝና ሱናን መከተል አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ለምክሮችና ልቦችን ለሚያለሰልሱ ነገሮች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. ከርሳቸው በኋላ ያሉት አራቱ የተመሩ ቅን ምትኮቻቸውን መከተል መታዘዙን እንረዳለን። እነሱም አቡ በከር፣ ዑመር፣ ዑሥማንና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው።
  4. በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር መከልከሉንና ሁሉም መጤ ነገር ጥመት መሆኑንም እንረዳለን።
  5. የአማኞችን ጉዳይ እንዲመራ ለተሾመ ሰው ከወንጀል ውጪ በሆኑ ጉዳዮች እርሱን መስማትና መታዘዝ እንደሚገባ እንረዳለን።
  6. አላህን በሁሉም ወቅትና ሁኔታ የመፍራትን አንገብጋቢነት እንረዳለን።
  7. በዚህ ኡመት ውስጥ ልዩነት ይከሰታል። በሚከሰት ወቅት ግን ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱና እና ወደ ቅን ምትኮቻቸው ሱና መመለስ ግድ ይላል።
ተጨማሪ