عن عُقبة بن عامر الجُهني رضي الله عنه قال: قال رسولُ الله صلَّى الله عليه وسلم:
«الجاهِرُ بالقرآن كالجاهِرِ بالصَّدَقَةِ، والمُسِرُّ بالقرآن كالمُسِرِّ بالصَّدَقَة».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي] - [سنن أبي داود: 1333]
المزيــد ...
ዑቅባ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 1333]
ቁርኣንን በይፋ የሚያነብ ምፅዋት በይፋ እንደሚሰጥ አምሳያ መሆኑን፤ ቁርኣንን በድብቅ የሚያነብ ምፅዋት በድብቅ እንደሚሰጥ አምሳያ መሆኑን ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ገለፁ።