+ -

عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«يقالُ لصاحبِ القرآن: اقرَأ وارتَقِ، ورتِّل كما كُنْتَ ترتِّل في الدُنيا، فإن منزِلَكَ عندَ آخرِ آية تقرؤها».

[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وأحمد] - [سنن أبي داود: 1464]
المزيــد ...

ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።"

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 1464]

ትንታኔ

ቁርኣንን ለሚያነብ፣ ቁርኣን ውስጥ ባለው ለሚሰራ፣ በቃሉ መሸምደድንም ሆነ አሳምሮ ማንበብን አጥብቆ የያዘ ጀነት በሚገባ ጊዜ "ቁርኣንን አንብብ! በዚህም ሰበብ የጀነት ደረጃዎችን ውጣ! ቁርኣንን በስክነትና እርጋታ ዱንያ ላይ ታነበው እንደነበርከው አንብብ! ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በቁጥርም ሆነ በሁኔታ ለሥራችን በሚመጥን መልኩ ነው የምንመነዳው።
  2. ቁርኣንን በማንበብ፣ አሳምሮ መቅራት፣ በመሸምደዱ፣ በማስተንተኑና በቁርኣን በመስራት ላይ መበረታታቱ።
  3. ጀነት በርካታ ደረጃዎችና እርከኖች ያሏት ሲሆን የቁርኣን ባለቤት የሆነ ሰው ከፍተኛ የሆነውን ደረጃ ነው የሚያገኘው።