ንዑስ ምድቦች

የሓዲሦች ዝርዝር

ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።
عربي እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ
ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።
عربي እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ
'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)
عربي እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ
ቁርኣንን የሚቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ትርንጎ ነው። ሽታዋም ምርጥ ነው። ጣዕሟም ምርጥ ነው። ቁርአንን የማይቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ተምር ነው። ሽታ የላትም ጣዕሟ ግን ጣፋጭ ነው።
عربي እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ
ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።
عربي እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ