عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ قَرَأَ حَرْفًا مِنْ كِتَابِ اللهِ فَلَهُ بِهِ حَسَنَةٌ، وَالْحَسَنَةُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا، لَا أَقُولُ {الم} حَرْفٌ، وَلَكِنْ {أَلِفٌ} حَرْفٌ، وَ{لَامٌ} حَرْفٌ، وَ{مِيمٌ} حَرْفٌ».
[حسن] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 2910]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።) (ይሄንን ስል) {አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።'"
[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2910]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማንኛውም ከአላህ መጽሐፍ አንድ ፊደል የሚቀራ ሙስሊም ለርሱ ምንዳ እንዳለውና አንዱ ምንዳ ደግሞ ለርሱ በአምሳያው እስከ አስር ድረስ እንደሚባዛለት ተናገሩ።
ከዚያም ይህንን ({አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።) በሚለው ንግግራቸው ሶስት ፊደል እንደሚሆኑና ሰላሳ ምንዳ እንደሚሆኑ ገለፁ።