عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «قَالَ اللَّهُ: كَذَّبَنِي ابْنُ آدَمَ وَلَمْ يَكُنْ لَهُ ذَلِكَ، وَشَتَمَنِي وَلَمْ يَكُنْ لَهُ ذَلِكَ، فَأَمَّا تَكْذِيبُهُ إِيَّايَ فَقَوْلُهُ: لَنْ يُعِيدَنِي، كَمَا بَدَأَنِي، وَلَيْسَ أَوَّلُ الخَلْقِ بِأَهْوَنَ عَلَيَّ مِنْ إِعَادَتِهِ، وَأَمَّا شَتْمُهُ إِيَّايَ فَقَوْلُهُ: اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا وَأَنَا الأَحَدُ الصَّمَدُ، لَمْ أَلِدْ وَلَمْ أُولَدْ، وَلَمْ يَكُنْ لِي كُفْؤًا أَحَدٌ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 4974]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አላህ እንዲህ አለ: የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር! እኔን ማስተባበሉማ ‹መጀመሪያ እንደፈጠረኝ (የትንሳኤ ቀን) አይመልሰኝም› ማለቱ ነው። በኔ ላይ እርሱን (የትንሳኤ ቀን) ከመመለስ ይልቅ መጀመሪያ መፍጠሩ ቀላል አይደለምን?። እኔን መስደቡማ ‹አላህ ልጅን ያዘ!› ማለቱ ነው። እኔ አንድ ነኝ፣ የሁሉ መጠጊያም ነኝ፣ አልወልድም፣ አልወለድም፣ ለኔም አንድም ቢጤ የለኝም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4974]
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ሐዲሠል ቁድስ ውስጥ አላህ ስለአጋርያንና ከሀዲዎች እነርሱ እንደሚያስተባብሉት፣ በጉድለትና ነውሮች እንደሚገልፁትና ይህም ለነርሱ እንደማይገባ መናገሩን ገለፁ።
አላህን ማስተባበላቸውም: አላህ ካልነበሩበት መጀመሪያ የፈጠራቸው ሲሆን ከሞቱ በኋላም ድጋሚ እንደማይመልሳቸው መሞገታቸው ነው። ምንም እንኳ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ስለሆነ መጀመሪያ መፍጠርም ይሁን ወደነበሩበት መመለስ ከአሏህ አንፃር እኩል ቢሆንም መጀመሪያ ካልነበሩበት የፈጠረ አምላክ እነርሱን በመመለስ ላይም ቻይ መሆኑን ነገራቸው።
አላህን መስደባቸውም: ለርሱ ልጅ አለው ማለታቸው ነው። በነርሱ ላይም እርሱ አንድ፣ በስሞቹ፣ በባህሪያቱና በድርጊቱ በሁሉም ምሉዕነት ብቸኛ የሆነ፤ ከሁሉም ጉድለትና ነውርም የጠራ፤ ከማንም የማይፈልግ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ግን ወደርሱ የሚፈልጉ የሆነ መጠጊያ፤ ለአንድም አካል ወላጅ ያልሆነ፤ ለአንድም አካል ልጅ ያልሆነ፤ ከአምሳያ ወይም ቢጤ አንዳችም የሌለኝ ነኝ። በማለት መለሰላቸው።