+ -

عَن عَبْدِ اللهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رضي الله عنهما أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، يَقُولُ:
«إِنَّ قُلُوبَ بَنِي آدَمَ كُلَّهَا بَيْنَ إِصْبَعَيْنِ مِنْ أَصَابِعِ الرَّحْمَنِ، كَقَلْبٍ وَاحِدٍ، يُصَرِّفُهُ حَيْثُ يَشَاءُ» ثُمَّ قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «اللهُمَّ مُصَرِّفَ الْقُلُوبِ صَرِّفْ قُلُوبَنَا عَلَى طَاعَتِكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2654]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ:
"የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል።" ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ "ቀልቦችን አዘዋዋሪ የሆንከው አላህ ሆይ! ቀልባችንን በአምልኮህ ላይ አዙረው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2654]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአደም ልጆች ሁሉ ቀልባቸው እንደ አንድ ቀልብ ከአርረሕማን ጣቶች በሁለት ጣቶቹ መካከል መሆናቸውን ተናገሩ። እንደፈለገውም ይገለባብጠዋል። ከፈለገ በሐቅ ላይ ያፀናዋል፤ ከፈለገም ከሐቅ ያጠመዋል። በሁሉም ቀልቦች ላይ የሚፈፅመው ማስተናበር የአንድ ሰውን ቀልብ እንደማስተናበር ነው። አላህን አንድ ጉዳይ ከሌላ ጉዳይ አያጠምደውም። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀጥለው ይህን ዱዓ አደረጉ "አንዳንዴ ወደ ትእዛዝህ፣ አንዳንዴ አንተን ወደ መወንጀል፣ አንዳንዴ አንተን ወደማውሳት፣ አንዳንዴ ደሞ አንተን ከማውሳት ወደ መዘናጋት ቀልቦችን የምትገለባብጥ አላህ ሆይ! ልባችንን ወደ አምልኮህ አዙረው።"

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቀደርን ማፅደቅ እንረዳለን። አላህ የባሮቹን ቀልብ በጻፈባቸው ውሳኔ ልክ ያዞራቸዋል።
  2. አንድ ሙስሊም በእውነትና ቅናቻ ላይ ጌታው እንዲያፀናው አዘውትሮ መጠየቅ ይገባዋል።
  3. አጋር በሌለው በአላህ ብቻ ቀልብን ማንጠልጠልና እርሱን ብቻ መፍራት እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. አጁርሪይ እንዲህ ብለዋል: "የሐቅ ባለቤቶች አላህ ነፍሱን በገለፀበት ነገር፣ መልክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህን በገለፁት ነገርና ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አላህን በገለፁት ነገር ይገልፁታል።" ይህ ሐቁን የተከተሉና አዲስ ነገር ያልፈጠሩ ዑለማዎች መንገድ ነው።" (ንግግራቸው ተጠናቀቀ)። አህሉ ሱናዎች አላህ ለነፍሱ ያፀደቀውን ስሞችና ባህሪያት ሳያጣምሙ፣ ትርጉም አልባ ሳያደርጉ፣ አኳኋኑን ሳይገልፁና ሳያመሳስሉ ለአላህ ያፀድቃሉ። አላህ ከራሱ ላይ ውድቅ ያደረገውንም ነገር ውድቅ ያደርጋሉ። ማፅደቅም ሆነ ውድቅ ማድረግ ላልመጣበት ጉዳይም ዝም ይላሉ። አላህ እንዲህ ብሏል: {የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱም ሰሚው ተመልካች ነው።}"