عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنَّ اللَّهَ قَالَ: مَنْ عَادَى لِي وَلِيًّا فَقَدْ آذَنْتُهُ بِالحَرْبِ، وَمَا تَقَرَّبَ إِلَيَّ عَبْدِي بِشَيْءٍ أَحَبَّ إِلَيَّ مِمَّا افْتَرَضْتُ عَلَيْهِ، وَمَا يَزَالُ عَبْدِي يَتَقَرَّبُ إِلَيَّ بِالنَّوَافِلِ حَتَّى أُحِبَّهُ، فَإِذَا أَحْبَبْتُهُ: كُنْتُ سَمْعَهُ الَّذِي يَسْمَعُ بِهِ، وَبَصَرَهُ الَّذِي يُبْصِرُ بِهِ، وَيَدَهُ الَّتِي يَبْطِشُ بِهَا، وَرِجْلَهُ الَّتِي يَمْشِي بِهَا، وَإِنْ سَأَلَنِي لَأُعْطِيَنَّهُ، وَلَئِنِ اسْتَعَاذَنِي لَأُعِيذَنَّهُ، وَمَا تَرَدَّدْتُ عَنْ شَيْءٍ أَنَا فَاعِلُهُ تَرَدُّدِي عَنْ نَفْسِ المُؤْمِنِ، يَكْرَهُ المَوْتَ وَأَنَا أَكْرَهُ مَسَاءَتَهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6502]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የምወደው ቢሆን እንጂ፤ የወደድኩትም ጊዜ የሚሰማበት መስሚያው እሆነዋለሁ፣ የሚያይበት መመልከቻ እሆነዋለሁ፣ የሚጨብጥበት እጅ እሆነዋለሁ፣ የሚራመድበት እግር እሆነዋለሁ፣ ቢጠይቀኝ እሰጠዋለሁ፣ ከኔ ጥበቃ ከፈለገ እጠብቀዋለሁ። እኔ ከማደርገው መካከል የሙእሚን ነፍስን ለመውሰድ እንደማመነታው በአንዳችም ነገር አላመነታሁም። እርሱ ሞትን ይጠላል እኔ ደግሞ እርሱን መጉዳት እጠላለሁ።›'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6502]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሐዲሠል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: ከወዳጆቼ መካከል አንድን የኔን ወዳጅ ያወከውና ያስቆጣው ከኔ ጋር ጠላት እንደሆነ አውጄያለሁም አሳውቄዋለሁም፤
"ወሊይ" (የአላህ ወዳጅ) የሚባለው: አላህን ፈሪ አማኝ ነው። አንድ ባሪያ ባለው ኢማንና አላህን ፈሪነት ልክ የአላህ ወዳጅነት ይኖረዋል። አንድ ሙስሊም አላህ ግዴታ ካደረገበት ትእዛዛትን መፈፀምና ክልክሎችን ከመተው በበለጠ ወደ ጌታው ተወዳጅ የሚሆንበት አንዳችም ነገር አይቃርበውም። አንድ ሙስሊም ወደ ጌታው ከግዴታዎች ጋር በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የአላህን ውዴታ የሚያገኝ ቢሆን እንጂ፤ አላህ የወደደው ጊዜ በነዚህ አራት አካላቱ ላይ ለርሱ አጋዥ ይሆነዋል።
በመስሚያው ያግዘዋል። አላህን ከሚያስደስት ነገር በቀር አይሰማም።
በመመልከቻው ያግዘዋል። ቢመለከተው አሏህ የሚወድለትንና የሚያስደስተውን ነገር እንጂ አይመለከትም።
በእጁም ያግዘዋል። በእጁ አላህን ከሚያስደስት ነገር በቀር አይሰራም።
በእግሩም ያግዘዋል። አላህን ወደሚያስደስት ነገር ካልሆነ በቀር አይራመድም። መልካም ነገር ወዳለበት ካልሆነ በቀር አይሮጥም።
ከዚህም ጋር አላህን አንዳች ነገር ከጠየቀው አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፤ ተማፅኖውንም የሚሰማው ይሆናል። በአላህ ጥበቃን ካስፈለገውና የአሏህን ከለላ ፈልጎ ከተጠጋ ጥራት የተገባው አላህም ከሚፈራው ነገር ይጠብቀዋል።
ቀጥሎም አላህ እንዲህ አለ: የሙእሚንን ነፍስ ስወስድ ለርሱ በማዘን እንደማመነታው እኔ ከምሰራው በአንዳችም ነገር አላመነታሁም። ምክንያቱም እርሱ ካለው ህመም አንፃር ሞትን ይጠላል። አላህ ደግሞ ሙእሚንን የሚያሳምም ነገር ይጠላል።