عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«اثْنَتَانِ فِي النَّاسِ هُمَا بِهِمْ كُفْرٌ: الطَّعْنُ فِي النَّسَبِ، وَالنِّيَاحَةُ عَلَى الْمَيِّتِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 67]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 67]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሰዎች መካከል ስለሚገኙ ሁለት የከሃዲያን ስራዎችና የድንቁርና ዘመን ስነ ምግባሮች ተናገሩ። እነርሱም:
የመጀመሪያው: ሰዎችን በዘራቸው መተቸት፣ ማሳነስና በዘር እነርሱ ላይ መኩራራት ነው።
ሁለተኛው: በመከራ ወቅት የአላህን ውሳኔ በማማረር ድምፅን ከፍ ማድረግ ወይም ከትእግስት ማጣት ብዛት ልብስን መቅደድ ነው።