+ -

عن أبي ذر رضي الله عنه:
عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِيمَا رَوَى عَنِ اللهِ تَبَارَكَ وَتَعَالَى أَنَّهُ قَالَ: «يَا عِبَادِي إِنِّي حَرَّمْتُ الظُّلْمَ عَلَى نَفْسِي، وَجَعَلْتُهُ بَيْنَكُمْ مُحَرَّمًا، فَلَا تَظَالَمُوا، يَا عِبَادِي كُلُّكُمْ ضَالٌّ إِلَّا مَنْ هَدَيْتُهُ، فَاسْتَهْدُونِي أَهْدِكُمْ، يَا عِبَادِي كُلُّكُمْ جَائِعٌ إِلَّا مَنْ أَطْعَمْتُهُ، فَاسْتَطْعِمُونِي أُطْعِمْكُمْ، يَا عِبَادِي كُلُّكُمْ عَارٍ إِلَّا مَنْ كَسَوْتُهُ، فَاسْتَكْسُونِي أَكْسُكُمْ، يَا عِبَادِي إِنَّكُمْ تُخْطِئُونَ بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَأَنَا أَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا فَاسْتَغْفِرُونِي أَغْفِرْ لَكُمْ، يَا عِبَادِي إِنَّكُمْ لَنْ تَبْلُغُوا ضَرِّي فَتَضُرُّونِي، وَلَنْ تَبْلُغُوا نَفْعِي فَتَنْفَعُونِي، يَا عِبَادِي لَوْ أَنَّ أَوَّلَكُمْ وَآخِرَكُمْ وَإِنْسَكُمْ وَجِنَّكُمْ كَانُوا عَلَى أَتْقَى قَلْبِ رَجُلٍ وَاحِدٍ مِنْكُمْ مَا زَادَ ذَلِكَ فِي مُلْكِي شَيْئًا، يَا عِبَادِي لَوْ أَنَّ أَوَّلَكُمْ وَآخِرَكُمْ وَإِنْسَكُمْ وَجِنَّكُمْ كَانُوا عَلَى أَفْجَرِ قَلْبِ رَجُلٍ وَاحِدٍ مَا نَقَصَ ذَلِكَ مِنْ مُلْكِي شَيْئًا، يَا عِبَادِي لَوْ أَنَّ أَوَّلَكُمْ وَآخِرَكُمْ وَإِنْسَكُمْ وَجِنَّكُمْ قَامُوا فِي صَعِيدٍ وَاحِدٍ فَسَأَلُونِي فَأَعْطَيْتُ كُلَّ إِنْسَانٍ مَسْأَلَتَهُ مَا نَقَصَ ذَلِكَ مِمَّا عِنْدِي إِلَّا كَمَا يَنْقُصُ الْمِخْيَطُ إِذَا أُدْخِلَ الْبَحْرَ، يَا عِبَادِي إِنَّمَا هِيَ أَعْمَالُكُمْ أُحْصِيهَا لَكُمْ ثُمَّ أُوَفِّيكُمْ إِيَّاهَا، فَمَنْ وَجَدَ خَيْرًا فَلْيَحْمَدِ اللهَ، وَمَنْ وَجَدَ غَيْرَ ذَلِكَ فَلَا يَلُومَنَّ إِلَّا نَفْسَهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2577]
المزيــد ...

ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ካለውና ከጠራው አላህ ባወሩት (ሐዲሠል ቁድሲይ) አላህ እንዲህ ብሏል: "ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ! ባሮቼ ሆይ! ከመራሁት በስተቀር ሁላችሁም ጠማማ ናችሁና ምራቻን ከኔ ጠይቁ እመራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! ካበላሁት በስተቀር ሁላችሁም ረሀብተኞች ናችሁና መብልን ከኔ ጠይቁ እመግባችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እኔ ካለበስኩት በስተቀር ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁና ልብስን ከኔ ጠይቁ አለብሳችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ በሌሊትም ሆነ በቀን ትሳሳታላችሁ። እኔ ደግሞ ሁሉንም ወንጀሎችን እምራለሁ። ስለሆነም ምህረትን ከኔ ፈልጉ እምራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ እኔን ጉዳትን ልትጎዱኝ አትችሉም። ጥቅምን ልትጠቅሙኝ ዘንድም አትችሉም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም ከናንተ መካከል እንደሚገኝ አንድ እጅግ አላህን ፈሪ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይጨምርም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም እንደ አንድ እጅግ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰው ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም በአንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ቢቆሙና ቢጠይቁኝ ለእያንዳንዱም የጠየቀኝን ብሰጠው መርፌ ባህር የገባች ጊዜ እንደምትቀንሰው ያህል ካልሆነ በቀር ይህ (መስጠቴ) እኔ ዘንድ ካለው (ሀብት) ምንም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ይህቺ ስራችሁ ናት ለናንተ አስቀምጥላችኋለሁ ከዚያም እራሷን እመነዳችኋለሁ። ምንዳውን መልካም ሆኖ ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከዛ ውጪ ሆኖ ያገኘ ግን ከነፍሱ በስተቀር ማንንም እንዳይወቅስ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2577]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በደልን በነፍሱ ላይ እርም እንዳደረገና አንዱ አንዱን እንዳይበድል በደልን በፍጡራኑ መካከልም እርም እንዳደረገው መናገሩን አብራሩ። ሁሉም ፍጡራን በአላህ መምራትና መግጠም ካልሆነ በቀር ከእውነተኛው መንገድ የጠመሙ ናቸው። መመራትን ከአላህ የጠየቀ ሰው አላህም ይገጥመዋል ይመራዋልም። ፍጡራን በሁሉም ጉዳዮቻቸው ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸው። አላህን የጠየቀን ሰው አላህም ጉዳዩን ይፈፅምለታል ይበቃዋልም። ፍጡራን ሌት ተቀን ወንጀል ይፈፅማሉ። አላህ ደግሞ ባሪያው ምህረትን በሚጠይቀው ወቅት ይሸሽገዋልም ያልፈዋልም። ፍጡራን አላህን አንዳችም ሊጎዱም ወይም ሊጠቅሙ አይችሉም። ፍጡራን ሁሉ እንደ አንድ አላህን እጅግ የሚፈራ ቀልብ ያለው ግለሰብ ቢሆኑ ፍራቻቸው በአላህ ንግስና ላይ አትጨምርም። ሁሉም እንደ አንድ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑም ጥመታቸው በንግስናው ላይ አንዳችም አይቀንስም። ምክንያቱም ደካሞችና ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸውና። በሁሉም ሁኔታ፣ ዘመንና ስፍራ ወደርሱ ፈላጊዎች ናቸው። የተብቃቃም እሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ሰዉም ጋኔኑም ከመጀመሪያቸው እስከመጨረሻቸው አላህን ለመጠየቅ በአንድ ስፍራ ላይ ቢቆሙና ከነርሱም ለእያንዳንዱ ሁሉ የጠየቀውን ቢሰጥ ይህ መስጠቱ አላህ ዘንድ ካለው አንዳችም አይቀንስም። ልክ እንደ መርፌ ባህር ውስጥ ገብታ ብትወጣ ባህሩ በዚህ አንዳችም እንደማይቀነሰው ማለት ነው። ይህም የሆነው ከተሟላው ሀብቱ አንፃር ነው። ጥራት ተገባው!
ጥራት የተገባው አላህ የባሮችን ስራዎች ይጠብቃልም ያስቀምጣልም። ከዚያም እሷኑ የትንሳኤ ቀን ይመነዳቸዋል። የስራውን ምንዳ መልካም ሆኖ ያገኘው ሰው አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ስለገጠመው አላህን ያመስግን። የስራውን ምንዳ ከዚህ ውጪ ሆኖ ያገኘ ሰውም ወደ ክስረት የመራችውን በመጥፎ የምታዘው ነፍሱን እንጂ ሌላን እንዳይወቅስ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው ከሚዘግቡት ሐዲሦች መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድስ ወይም ሓዲሠል ኢላሂይ በመባልም ይጠራል። ይህም ቃሉም ሆነ መልዕክቱ ከአላህ የሆነ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ የቁርአን መለዮች የሉትም። ለምሳሌ: - በማንበቡ (ሓሰና የሚያስገኝ) አምልኮን መፈፀም፣ ለሱ ጦሀራ ማድረግ ፣ የሱን አምሳያ ከቻላቹ አምጡ የተባለለት ተዓምራዊነቱና ሌሎችም ቁርአን የተለየበት መለዮዎች ይጠቀሳሉ።
  2. ባሮች የሚጎናፀፉት እውቀትና መመራት በአላህ መምራትና ማሳወቅ ነው።
  3. አንድ ባሪያ የሚያገኘው መልካም ነገር በአላህ ችሮታ ነው። የሚያገኘው መጥፎ ነገር ግን በነፍሱና በስሜቱ ሳቢያ ነው።
  4. መልካምን የሰራ በአላህ መግጠም ነው። የአላህ መመንዳትም ከአላህ የሆነ ችሮታ ስለሆነ ምስጋናው ለአሏህ ነው። መጥፎን የሰራ ግን ከነፍሱ በቀር ማንንም እንዳይወቅስ።
ተጨማሪ