عن الْأَغَرِّ رضي الله عنه، وَكَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يَا أَيُّهَا النَّاسُ تُوبُوا إِلَى اللهِ، فَإِنِّي أَتُوبُ فِي الْيَوْمِ إِلَيْهِ مِائَةَ مَرَّةٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2702]
المزيــد ...
ከአልአገርሪ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2702]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች ተውበትና ምህረት መጠየቅን እንዲያበዙ አዘዙ። እርሳቸው የቀደመውም ሆነ የወደፊት ወንጀላቸው የተማረ ከመሆኑም ጋር እሳቸውም በቀን ከመቶ ጊዜ በላይ ወደ አላህ ተውበት እንደሚያደርጉና ምህረት እንደሚጠይቁ ተናገሩ። ይህም ለአላህ ያላቸውን የተሟላ መዋደቅና የተሟላ ባርነትን የሚያሳይ ነው።