عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَاللهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ، وَمَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ، وَمَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللهِ وَيَتَدَارَسُونَهُ بَيْنَهُمْ إِلَّا نَزَلَتْ عَلَيْهِمِ السَّكِينَةُ، وَغَشِيَتْهُمُ الرَّحْمَةُ، وَحَفَّتْهُمُ الْمَلَائِكَةُ، وَذَكَرَهُمُ اللهُ فِيمَنْ عِنْدَهُ، وَمَنْ بَطَّأَ بِهِ عَمَلُهُ لَمْ يُسْرِعْ بِهِ نَسَبُهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2699]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2699]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም አላህ ዘንድ የሚመነዳው ከሙስሊሞች ጋር ከሚሰራው የስራ አይነት አንፃር እንደሆነ ገለፁ። ከአንድ አማኝ ላይ ከዱንያ ችግሮች መካከል አንድን ችግርና መከራ ያቀለለ፣ የገላገለ፣ ያስወገደና ያነሳ ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮች መካከል አንድን ችግሩን በማቅለል ይመነዳዋል። ለተቸገረ ያቀለለ፣ ያገራ፣ ችግሩንም ያስወገደ አላህም ለርሱ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ጉዳዩን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር - ለምሳሌ ለርሱ ግልፅ መውጣት የማይገባውን ስህተትና ጥፋት አይቶ - የሸሸገ ሰው አላህ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን ዲናዊም ይሁን ዱንያዊ ጥቅሞቹ ላይ እስካገዘው ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ይሆናል። ማገዝ በዱዓ፣ በአካል፣ በገንዘብና ከዚህም ውጪ ባሉ ነገሮች ይፈፀማል። የአላህን ፊት ፈልጎበት ሸሪዓዊ ዕውቀትን ለማግኘት የተጓዘን ሰው ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ አላህ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ዘንድ ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በነርሱ ላይ እርጋታና ስክነት ይሰፍናል፤ የአላህ እዝነትም ይሸፍናቸዋል፤ መላዕክቶች ያካብቧቸዋል፤ አላህ ዘንድ ቅርብ ከሆኑት ጋር ያሞግሳቸዋል (ያወድሳቸዋል)። ከክብር አላህ ባሪያውን በላይኛው አለም ማውሳቱ ብቻ በቂ ነው። ስራው ጎዶሎ የሆነ ሰው የተሟላ ስራ የሰሩ ሰዎች ደረጃ ላይ አይደርስም። ስለዚህ በዘር ልቅናና በወላጆች ደረጃ ተማምኖ መልካም ስራን ማጓደል አይገባም።