+ -

عَنْ عَائِشَةَ رضي الله عنها قَالَتْ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ» متفق عليه. ولمسلم: «مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2697]
المزيــد ...

ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእዛዛችን) የሌለን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው እርሱ (የፈጠረው አዲስ ነገር) ተመላሽ ነው።›" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። በሙስሊም ዘገባ "ትእዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው እርሱ (ሥራው) ተመላሽ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2697]

ትንታኔ

በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አምልኮ የተመሰረተው በቁርአንና ሐዲሥ ላይ በመጣው ላይ ስለሆነ አላህን የምናመልከው በደነገገው ድንጋጌ መሰረት እንጂ በተፈጠሩና በተፈበረኩ አምልኮዎች አይደለም።
  2. የኢስላም ሃይማኖት ተግባራዊነት በግላዊ ምልከታና አንድን ነገር መልካም አድርጎ በማየት ሳይሆን መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል ነው።
  3. ይህ ሐዲሥ የኢስላምን ምሉእነት የሚጠቁም ነው።
  4. ቢድዓ (መጤ) ማለት: በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመንና በሶሐቦች ዘመን ያልነበረ ሁሉም በሃይማኖት ውስጥ የተፈጠረ እምነታዊ ጉዳይ ወይም ንግግር ወይም ተግባር ነው።
  5. ይህ ሐዲሥ ከኢስላም መሰረቶች መካከል አንድ መሰረት የሆነና ለተግባራቱም እንደሚዛን የሆነ ሐዲሥ ነው። የትኛውም የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ስራ ባለቤቱ በስራው ምንዳ እንደማያገኝበት ሁሉ ልክ እንደዚሁ መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይዘው የመጡትን ያልገጠመ የትኛውም ስራም በባለቤቱ ላይ ተመላሽ ይሆናል።
  6. የተከለከለው አዲስ ፈጠራ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ነው እንጂ አለማዊ ጉዳይ ላይ አይደለም።