عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ دَعَا إِلَى هُدًى كَانَ لَهُ مِنَ الْأَجْرِ مِثْلُ أُجُورِ مَنْ تَبِعَهُ، لَا يَنْقُصُ ذَلِكَ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا، وَمَنْ دَعَا إِلَى ضَلَالَةٍ كَانَ عَلَيْهِ مِنَ الْإِثْمِ مِثْلُ آثَامِ مَنْ تَبِعَهُ، لَا يَنْقُصُ ذَلِكَ مِنْ آثَامِهِمْ شَيْئًا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2674]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው። ወደ ጥመት የተጣራ ሰውም የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ወንጀል ይኖርበታል። ይህም (በርሱ ላይ የሚኖረው ወንጀል) ከወንጀሎቻቸው ምንም ሳይቀነስ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2674]
በንግግሩ ወይም በተግባሩ እውነትና መልካም ወዳለበት መንገድ ሰዎችን የመራ፣ የጠቆመና የቀሰቀሰ ሰው የተከታዩን አምሳያ ምንዳ እንደሚያገኝና ይህም ከተከታዩ ምንዳ አንዳችም ሳይቀነስ እንደሆነ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። በንግግር ወይም በተግባር ወንጀልና ኃጢአት ወይም የማይፈቀድ ነገር ወዳለበት የጥመትና የክፋት መንገድ ሰዎችን የጠቆመ ሰውም የተከታዩን አምሳያ ወንጀልና ኃጢአት ይኖርበታል። ይህም ከነርሱ ወንጀል አንዳችም ሳይቀነስ ነው።