عَنْ سَلَمَةَ بْنِ الْأَكْوَعِ رضي الله عنه:
أَنَّ رَجُلًا أَكَلَ عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِشِمَالِهِ، فَقَالَ: «كُلْ بِيَمِينِكَ»، قَالَ: لَا أَسْتَطِيعُ، قَالَ: «لَا اسْتَطَعْتَ»، مَا مَنَعَهُ إِلَّا الْكِبْرُ، قَالَ: فَمَا رَفَعَهَا إِلَى فِيهِ.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2021]
المزيــد ...
ከሰለማ ቢን አክወዕ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦
"አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት። ኩራት እንጂ ሌላ አልከለከለውም። ሰለማ እንዲህ አለ '(ከዛ በኃላ) እጁን ወደ አፉ ማንሳት አልቻለም።' "
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2021]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሰው በግራ እጁ ሲበላ ተመለከቱትና በቀኝ እጁ እንዲበላ አዘዙት። ሰውዬውም በኩራትና በውሸት በቀኝ እጁ መብላት እንደማይችል መለሰላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በቀኝ እጁ መመገብ አሏህ እንዳያስችለው በርሱ ላይ ዱዓ አደረጉበት። ቀኝ እጁን ሽባ በማድረግ አላህ የነቢዩን ዱዓ ተቀበለ። ከዚህ በኋላም ምግብ ወይም መጠጥ ወደ አፉ ማንሳት አልቻለም።