عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ:
كُنَّا مَعَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِذْ سَمِعَ وَجْبَةً، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «تَدْرُونَ مَا هَذَا؟» قَالَ: قُلْنَا: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ، قَالَ: «هَذَا حَجَرٌ رُمِيَ بِهِ فِي النَّارِ مُنْذُ سَبْعِينَ خَرِيفًا، فَهُوَ يَهْوِي فِي النَّارِ الْآنَ حَتَّى انْتَهَى إِلَى قَعْرِهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2844]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለን ድንገት አስደንጋጭ ድምፅ ሰሙ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሉ። እኛም "አላህና መልክተኛው አዋቂዎች ናቸው።" አልን። እርሳቸውም " ይህ ከሰባ አመት ጀምሮ እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ነው። እርሱም እሳት ውስጥ ወደ ጥልቀቷ መጨረሻ ዛሬ እስኪደርስ ድረስ እየተምዘገዘገ ነበር።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2844]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሆነ ነገር ሲወድቅ የሚሰማውን አይነት አስደንጋጭ ድምፅ ሰሙ። እርሳቸው ዘንድ ያሉትንም ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ስለዚህ ድምፅ ምንነት ጠየቋቸው። ሶሐቦቹም "አላህና መልክተኛው አዋቂዎች ናቸው።" አሉ።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: ይህ የሰማችሁት ድምፅ ከሰባ አመት ጀምሮ ከጀሀነም ጫፍ የተወረወረ ድንጋይ ነው። ድምፁን በሰማችሁበት ጊዜ ወደ መጨረሻ ጥልቀቷ እስከደረሰበት የዛሬዋ ቀን ድረስ እየወረደና እየተምዘገዘገ ነበር።