+ -

عَنْ مُصْعَبِ بْنِ سَعْدٍ قَالَ: رَأَى سَعْدٌ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ لَهُ فَضْلًا عَلَى مَنْ دُونَهُ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«هَلْ تُنْصَرُونَ وَتُرْزَقُونَ إِلَّا بِضُعَفَائِكُمْ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 2896]
المزيــد ...

ከሙስዐብ ቢን ሰዕድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ሰዕድ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ደረጃ እንዳለው ተሰማው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉት:
"የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል። - ቲርሚዚ ዘግበውታል። - An-Nasaa’i - አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2896]

ትንታኔ

ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ራሱን በጀግንነትና በመሳሰሉት ምክንያት ከርሱ በታች ካሉ ደካማ ሰዎች የበለጠ አድርጎ አሰበ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "በደካሞቻችሁ፣ በነርሱ ዱዓ፣ ሶላትና ኢኽላስ ካልሆነ በቀር ትረዳላችሁን? ትቀለባላችሁን?" አሉ። አብዛኛው ጊዜ ደካማዎች ዱዓቸውን እጅግ ለአላህ አጥርተው፣ አምልኳቸውንም እጅግ ተመስጠው ነው የሚፈፅሙት። ይህም ቀልባቸው በዱንያ ጌጣጌጥ ከመንጠልጠል የፀዳ ስለሆነ ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመተናነስ ላይ መነሳሳቱንና በሌሎች ላይ ከፍ ከፍ ከማለት መከልከሉን እንረዳለን።
  2. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ጠንካራው በጀግንነቱ ስለሚሻል ከደካሞች ቢበልጥ ደካማው ደግሞ በዱዓውና ስራውን ለአላህ አጥርቶ በመስራቱ ስለሚሻል ከጠንካራው ይበልጣል።"
  3. ለድሃዎች በጎ በማድረግና ሐቃቸውን በመስጠት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህን ማድረግህ አላህ እንዲያዝንልህና እንዲረዳህ የሚያደርግ አንዱ ምክንያት ነውና።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ