عن بعض أزواج النبي صلى الله عليه وسلم عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ أَتَى عَرَّافًا فَسَأَلَهُ عَنْ شَيْءٍ لَمْ تُقْبَلْ لَهُ صَلَاةٌ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2230]
المزيــد ...
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆኑት መካከል ከአንዷ እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2230]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር ከመሄድ አስጠነቀቁ። (ይህም ጠንቋይን፣ ኮኮብ እየተመለከቱ የሚተነብዩን፣ ጠጠርን ተንተርሰው የሚተነብዩንና የመሳሰሉትን የሩቅ እውቀትን ለመሞገት ለመነሻ ያህል የሚጠቀሙን የሚያጠቃልል የወል ስም ነው።) የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር በመሄድ ሩቅ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዳችን መጠየቁ ብቻ በሱ ሳቢያ የአርባ ቀን የሶላቱን ምንዳ አላህ ይከለክለዋል። ይህም በዚህ ትልቅ ወንጀሉና ሀጢዐቱ ምክንያት መቀጣጫ እንዲሆነው ነው።