عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«من اقتبَسَ علْمًا مِنَ النُّجُومِ اقْتبَسَ شُعبَة مِن السِّحرِ، زادَ ما زادَ».
[صحيح] - [رواه أبو داود وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 3905]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3905]
የኮኮብ እውቀትን፣ የኮኮቦች እንቅስቃሴ፣ አገባብና አወጣጥን እውቀት የእከሌን መሞት ወይም ህያው መሆን ወይም መታመሙና የመሳሰሉትን ለወደፊት የሚከሰቱ ምድራዊ ክስተቶች ላይ ማስረጃ ለማድረግ የተማረ ሰው በርግጥም ከፊል ጥንቆላን ቀስሟል። ይህንኑ እውቀት ባበዛ ቁጥር ጥንቆላንም በርግጥ አብዝቷል በማለት ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።