+ -

عن عمران بن حصين رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«‌لَيْسَ ‌مِنَّا ‌مَنْ ‌تَطَيَّرَ أَوْ تُطُيِّرَ لَهُ، أَوْ تَكَهَّنَ أَوْ تُكُهِّنَ لَهُ، أَوْ سَحَرَ أَوْ سُحِرَ لَهُ، وَمَنْ عَقَدَ عُقْدَةً، وَمَنْ أَتَى كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ».

[حسن] - [رواه البزار] - [مسند البزار: 3578]
المزيــد ...

ከዒምራን ቢን ሑሰይን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
'የገድ ተግባርን የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት፣ ወይም የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ፣ ወይም የደገመ ወይም ያስደገመ፣ ትብታብንም የተበተበ ከኛ አይደለም። ጠንቋይ ዘንድ የሄደና የሚናገረውን ነገር አምኖ የተቀበለ በሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው ነገር በእርግጥ ክዷል።'"

[ሐሰን ነው።] - [በዛር ዘግበውታል።] - [ሙስነድ በዛር - 3578]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ውስጥ አንዳንድ ተግባራት የፈፀሙ ሰዎችን "ከኛ አይደሉም!" በማለት ዛቱ። ከተግባራቱም፦
የመጀመሪያው: "ገድ ተግባር የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት" የዚህ አመለካከት መሰረት:- ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያለን ስራ ለመጀመር በራሪን ይለቃል፤ በራሪው ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ተስፋን በመሰነቅ ወደ ሚፈልገው አላማ ይሄዳል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ገደ ቢስነትን በማመን የሚፈልገውን አላማ ከመፈፀም ይቆጠባል። ይህን ተግባር ራሱም ይሁን ለርሱ የሚሰራለትን በመመደብም መፈፀም አይፈቀድም። በማንኛውም በራሪዎች ወይም እንስሳዎች ወይም በአካል ጉዳተኞች ወይም በቁጥሮች ወይም በቀናት ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ በሚሰማም ይሁን በሚታይ በሆነ ነገር ገደ ቢስነትን ማመን እዚህ ውስጥ ይካተታል።
ሁለተኛው: "የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ።" ከዋክብትንና ሌሎች ነገሮችን በመጠቀም የሩቅ እውቀትን የሞገተ ሰው ወይም እንደ ጠንቋይና የመሳሰሉት የሩቅን እውቀት ወደ ሚሞግቱ ሰዎች የሄደና የሩቅን እውቀት ሞግቶ በሚናገረው ያመነ በሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው በርግጥ ክዷል።
ሶስተኛ: "የደገመ ወይም የተደገመለት" እሱም አንድን ሰው ሊጠቅም ወይም ሊጎዳ የድግምትን ተግባር በራሱ የፈፀመ ወይም ለሱ ድግምት የሚሰራለትን የመደበ ሰው ወይም ትብታብን ተብትቦ የቋጠረና ክልክል የሆኑ መነባንቦችን በማነብነብና እርሱ ላይ በመትፋት የደገመበት ሰው ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ ላይ መመካትና በአላህ ውሳኔና ፍርድ ማመን ግዴታ መሆኑን፤ የገድ፣ የገደቢስነት፣ የጥንቆላ ፣ የድግምት እምነት ወይም ባለቤቶቹን ስለነዚህ ጉዳይ መጠየቅ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. የሩቅ እውቀትን መሞገት ተውሒድን የሚፃረር የሆነ ሺርክ ነው።
  3. ጠንቋዮችን ማመንም ወደነርሱ መሄድም ክልክል ነው። እንዲሁ ለማወቅ በሚል ሰበብ ብቻ እንኳ መዳፍና ሲኒን ማንበብ፣ ኮኮብ ማየት ከጥንቆላ ውስጥ ይካተታል።
ተጨማሪ