عن عائشة رضي الله عنها قالت:
سَأَلَ أُنَاسٌ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الْكُهَّانِ، فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَيْسُوا بِشَيْءٍ» قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، فَإِنَّهُمْ يُحَدِّثُونَ أَحْيَانًا بِالشَّيْءِ يَكُونُ حَقًّا، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «تِلْكَ الْكَلِمَةُ مِنَ الْحَقِّ يَخْطَفُهَا الْجِنِّيُّ فَيَقُرُّهَا فِي أُذُنِ وَلِيِّهِ قَرَّ الدَّجَاجَةِ، فَيَخْلِطُونَ فِيهَا أَكْثَرَ مِنْ مِائَةِ كَذْبَةٍ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"ሰዎች የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለጠንቋዮች ጠየቁ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነርሱ 'ምንም አይደሉም።' በማለት መለሱ። እነሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ተናግረው እውነት ይሆናል።' አሉ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ' ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለወደፊት ስለሚከሰቱ የሩቅ ሚስጥራት ስለሚናገሩ ሰዎች ተጠየቁ። እሳቸውም: ቦታ አትስጡት ፤ ንግግራቸውን አትያዙ፤ ጉዳያቸው አያሳስባችሁ አሉዋቸው።
ሶሐቦችም "በእንዲህ ወርና በእንዲህ ቀን" ብለው የሩቅ ሚስጥር ጉዳይ እንደሚከሰት እንደሚናገሩና እንደተናገሩት ገጥሞ መከሰቱን አይነት ንግግራቸው አንዳንድ ጊዜ ተጨባጩን የሚገጥም መሆኑን ተናገሩ።
ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም እንዲህ ብለው መለሱላቸው "ጂኖች ከሰማይ የሚሰሙትን ወሬ በመስረቅ ወደ ጠንቋይ ወዳጆቻቸው አውርደው የሰሙትን ይነግሯቸዋል። ከዚያም ጠንቋዩ ከሰማይ በሰማው ላይ መቶ ውሸት ይጨምርበታል።"

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጠንቋዮችን ማመን መከልከሉን ፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ቢናገሩ እንኳ የሚናገሩት ነገር ውሸትና ቅጥፈት መሆኑን እንረዳለን።
  2. ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመላካቸው ምክንያት ከተወርዋሪ ኮኮብ አምልጦ ወሬ የሰረቀ ጂን ካልሆነ በቀር ሰይጣናት ከወሕይም ይሁን ሌላ እንዳይሰሙ ሰማይ ተጠብቃለች።
  3. ጂኖች ከሰው የሆነ ወዳጅ እንደሚይዙ እንረዳለን።