عن أنس رضي الله عنه قال:
كُنَّا عِنْدَ عُمَرَ فَقَالَ: «نُهِينَا عَنِ التَّكَلُّفِ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 7293]
المزيــد ...

ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ዑመር ዘንድ ነበርንና እንዲህ አሉ: 'ከአቅም በላይ ከመጣጣር ተከልክለናል።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7293]

ትንታኔ

ዑመር -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ነገርን ንግግርም ይሁን ድርጊት የግድ መቸጋገር ሳያስፈልግ መቸገር ያለበትን ነገር ከመጠቀም እንደከለከሏቸው ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከተከለከሉት ከአቅም በላይ መጣጣር ውስጥ : - ጥያቄ ማብዛት ወይም በርሱ እውቀት በሌለው ነገር ያለአቅሙ መጣጣር ወይም አላህ ያሰፋው ጉዳዩ ላይ ማካበድ ይጠቀሳሉ።
  2. ሙስሊም የሆነ ሰው በንግግሩ፣ በተግባሩ፣ በአመጋገቡ፣ በአጠጣጡና በማንኛውም ሁኔታው ገራገርነትንና አለማካበድን ለነፍሱ ማለማመድ ይገባዋል።
  3. ኢስላም ገር እምነት መሆኑን እንረዳለን።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (62)